ስለ ሥጋዌ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ሥጋዌ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ቃል ሥጋ ሆነ፤ በመካከላችንም ዐደረ፤ እኛም ጸጋና እውነት የተሞላውን ከአብ ዘንድ ያለውን የአንድያ ልጁን ክብር አየን፡፡
እርሱም የመለኮት ባሕር ነበረው፥ ነገር ግን ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል የሚያደርጋውን የመለኮት ባሕይ እንደ ያዘ አልቆጠረም። ክብሩን ትቶ ራሱን ባዶ አደረገ። የባሪያንም መልክ ያዘ፤ በሰው አምሳል ተገለጠ፤ እንደ ሰውም ሆኖ በትህትና ራሱን ዝቅ አደረገ።
ነገር ግን በትክክለኛው ጊዜ እግዚአብሔር በህግ ሥር ያሉትን
ስለዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ በሥጋና ደም ስለሆኑ፣ በሞቱ አማካይነት ሞት ላይ ሥልጣን ያለውን ማለትም ዲያብሎስን ለመሻር ኢየሱስም እንደ እነርሱ ሥጋ ለብሶ።
እኛ ሁላችን በዚህ እንስማማለን፡- ‹‹የተገለጠው እግዚአብሔርን የመምሰል ምስጢር ታላቅ ነው፣›› ይህም በሥጋ የተገለጠው፣ በመንፈስ የጸደቀው፣ በመላእክት የታየው፣ በሕዝቦች መካከል የታወጀው፣ በዓለም የታመነው፣ በክብር ወደ ሰማይ ያረገ ነው፡፡
በሥጋ ድካም ምክንያት ሕግ ሊፈጽመው ያልተቻለውን እግዚአብሔር ፈጽሞታል። እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአታዊ ሥጋ ምሳሌ ለኃጢአት መሥዋዕት ይሆን ዘንድ ልኮ ኃጢአትን በሥጋው ኮነነ።
በእርሱ ድኽነት እናንተ ባለጠጎች ትሆኑ ዘንድ ፥ እርሱ ባለ ጠጋ ቢሆንም እንኳ ስለ እናንተ ደኸየ።
የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ እናውቃለን፣- ጌታ ኢየሱስ በሥጋ እንደመጣ የሚቀበል መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው።