ስለ ቃል (ሎጎስ) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ቃል (ሎጎስ) የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 ዮሐንስ 1:1
በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ፤
02 ዮሐንስ 1:14
ቃል ሥጋ ሆነ፤ በመካከላችንም ዐደረ፤ እኛም ጸጋና እውነት የተሞላውን ከአብ ዘንድ ያለውን የአንድያ ልጁን ክብር አየን፡፡
ደም የተነከረ ልብስ ለብሶ ነበር፤ ስሙ የእግዚአብሔር ቃል ተብሎ ይጠራል።
04 1ኛ ዬሐንስ 1:1
ከመጀመሪያው ስለ ነበረው፣ ስለ ሰማነው፣ በዓይኖቻች ስላየነው፣ ስለ ተመለከትነው ፣በእጆቻችንም ስለ ዳሰስነው ስለ ህይወት ቃል
05 ዕብራዊያን 1:2
አሁን ግን የሁሉም ነገር ወራሽ ባደረገው፣ ዓለምንም በፈጠረበት በልጁ ተናገረን።
06 ዮሐንስ 1:2-3
ይህም ቃል ከመጀመሪያው ከእግዚአብሔር ጋር ነበር፡፡ ሁሉም ነገር የተሠራው በእርሱ አማካይነት ነው፤ ከተሠሩት ነገሮች ሁሉ ያለ እርሱ የተሠራ አንድም ነገር አልነበረም፡፡
ያህዌ ሰማያትን በቃሉ የሰማይ ሰራዊትን በአፉ እስትንፋስ ፈጠረ፡፡
08 ቆላስይስ 1:16
ምክንያቱም በሰማያትና በምድር፤ የሚታዩትና የማይታዩት ነገሮች ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋል። ዙፋናትም ሆኑ ኅይላት ወይም ግዛቶችች ወይም ሥልጣናት፤ሁሉም ነገር በእርሱና ለእርሱ ተፈጥረዋል።