ስለ በቅንነት መመላለስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ በቅንነት መመላለስ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

አምላካችን ያህዌ ፀሐይና ጋሻችን ነውና፤ ያህዌ ጸጋንና ክብርን ይሰጣል፤ በቅንነት የሚሄዱትን መልካም ነገር አይነፍጋቸውም፡፡

ያህዌ ሆይ፣ በድንኳንህ ውስጥ የሚያድር ማን ነው? በተቀደሰው ኮረብታህስ የሚኖር ማን ነው? አካሄዱ ንጹሕ የሆነ፣ ጽድቅን የሚያደርግ ከልቡ እውነትን የሚናገር፤

03 ምሳሌ 2:7

እርሱ ደስ ለሚያሰኙት ጥልቅ ጥበብን ያከማቻል፣ ያለ ነቀፋ ለሚሄዱ ጋሻ ነው፣

04 ምሳሌ 28:18

በሐቀኝነት የሚራመድ ሰው በደህና ይጠበቃል፣ መንገዱ በጠማማነት የተሞላ ግን በድንገት ይወድቃል፡፡

ሰው ሆይ፣ መልካሙን፣ ያህዌ ከአንተ የሚፈልገውን ነግሮሃል ፍትሕ አድርግ፤ ደግነትን ውደድ፤ ከአምላክህ ጋር በትሕትና ተመላለስ፡፡

06 ምሳሌ 10:9

በሀቀኝነት የሚሄድ ሰው ተማምኖ ይሄዳል፣ መንገዱን የሚያጣምም ግን ይጋለጣል፡፡

በክፉዎች ምክር የማይሄድ በኃጢአተኞች መንገድ የማይቆም በፌዘኞች ወንበር የማይቀመጥ ምስጉን ነው፡፡

08 ምሳሌ 11:3

የቅኖች ሀቀኝነታቸው ይመራቸዋል፣ የከዳተኞች ጠማማ መንገድ ግን ራሳቸውን ያጠፋቸዋል፡፡

መንገዳቸው ነቀፋ የሌለበት በያህዌም ሕግ የሚሄዱ የተባረኩ ናቸው፡፡

10 ምሳሌ 14:2

በጽድቅ የሚሄድ ሰው እግዚአብሔርን ይፈራል፣ በመንገዱ ታማኝ ያልሆነ ግን ይንቀዋል፡፡

ጻድቅን ሰው ተመልከት ቅን የሆነውንም ሰው እይ የሰላም ሰው ተስፋ አለውና፡፡

12 ኢሳይያስ 33:15-16

በጽድቅ የሚሄድ ቅን ነገርንም የሚናገር፤ በሽንገላ የሚገኝ ትርፍን የሚንቅ፥ መማለጃ ጉቦን ከመጨበጥ እጁን የሚያርቅ፣ ደም የማፍሰስ ወንጀልን ከመስማት ጆሮቹን የሚያደነቍር፣ ክፋትንም ከማየት ዓይኖቹን የሚጨፍን ነው። እርሱ ከፍ ባለ ስፍራ ይቀመጣል፣ ጠንካራ አምባ መጠጊያው ይሆናል፣ እንጀራም ይሰጠዋል፣ ውኃውም የታመነች ትሆናለች።

13 ምሳሌ 20:7

ጽድቅን የሚያደርግ ሰው በሐቀኝነቱ ይራመዳል፣ ፍለጋውን የሚከተሉ ልጆቹም ደስተኞች ናቸው፡፡

14 ምሳሌ 13:6

በመንገዳቸው ያለ ነቀፋ የሚሄዱትን ጽድቅ ትጠብቃቸዋለች፣ ክፋት ግን ኃጢአተኞችን ትጥላቸዋለች፡፡

15 1ኛ ዬሐንስ 1:7

እርሱ ብርሃን እንደሆነ ፣ በብርሃን ብንመለላለስ እርስ በርሳችን ህብረት ይኖረናል፡፡የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስም ደም ከሃጢአት ሁሉ ያነጻናል።

ተዛማጅ ርዕሶች