ስለ ሐቀኝነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ሐቀኝነት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ምሳሌ 12:22

እግዚአብሔር ሀሰተኛ ከንፈሮችን ይጠላል፣ በእውነተኛነት በሚኖሩ ሰዎች ግን ደስ ይለዋል፡፡

02 ምሳሌ 11:1

እግዚአብሔር ትክክለኛ ያልሆነ ሚዛን ይጠላል፣ በትክክለኛ ሚዝን ግን ሚዛን ደስ ይለዋል፡፡

03 ኤፌሶን 4:25

ውሸትን አስወግዱ፤ ሁላችንም የአንድ አካል ብልቶች ስለሆንን «እያንዳንዱ ከባልንጀራው ጋር እውነትን ይነጋገር»።

04 ዘካርያስ 8:16

እናንተ ማድረግ ያለባችሁ እነዚህን ነው፤ እርስ በርሳችሁ እውነትን ተነጋገሩ፤ በአደባባዮቻችሁም እውነትን፣ ፍትሕንና ሰላምን አስፍኑ።

05 2ኛ ቆሮንቶስ 8:21

በጌታ ፊት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በሰዎች ፊት ደግሞ የከበረውን ነገር ለማድረግ እንተጋለን።

06 ምሳሌ 16:13

ንጉስ እውነትን በሚናገሩ ከንፈሮች ደስ ይለዋል፣ በግልጽነት የሚናገረውንም ሰው ይወደዋል፡፡

07 ቆላስይስ 3:9

አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋር አውልቃችሁ ስለ ጣላችሁ፣ አንዳችሁ በሌላው ላይ አትዋሹ።

አትስረቁ፡፡ አትዋሹ፡፡ አንዳችሁ ሌላችሁን አታታሉ፡፡

09 ምሳሌ 19:1

በንግግሩ ጠማማ ከሆነና ከሞኝ ሰው ይልቅ በሃቀኝነት የሚራመድ ድሃ ሰው ይሻላል፡፡

10 ዕብራዊያን 13:18

በሁሉም ነገር የከበረ ሕይወት ለመኖር የሚፈልግ ንጹሕ ኅሊና ስላለን ጸልዩልን።

11 ምሳሌ 24:26

እውነተኛ መልስ የሚሰጥ ሰው ከንፈሮችን ይስማል፡፡

12 ሮሜ 12:17

ክፉ ላደረገባችሁ ለማንም ክፉ አትመልሱ። በሰዎች ሁሉ ፊት መልካምን ነገር አድርጉ።

13 ምሳሌ 20:23

እኩል ያልሆኑ ሚዛኖችን እግዚአብሔር ይጠላል፣ ሐሰተኛ መስፈሪያም መልካም አይደለም፡፡

እንግዲያስ አንደበትህን ከክፉ ከልክል ከንፈርህንም ከውሸት ጠብቅ፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች