ስለ ቅንነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ቅንነት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
በሀቀኝነት የሚሄድ ሰው ተማምኖ ይሄዳል፣ መንገዱን የሚያጣምም ግን ይጋለጣል፡፡
የቅኖች ሀቀኝነታቸው ይመራቸዋል፣ የከዳተኞች ጠማማ መንገድ ግን ራሳቸውን ያጠፋቸዋል፡፡
አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና ታማኝነትና ቅንነት ይጠብቁኝ
እናንተን ትክክል አድርጎ መቀበል ከእኔ ይራቅ፤ እስክሞት ድረስ ትክክለኛነቴን በፍጹም አልጥልም።
ጽድቅን የሚያደርግ ሰው በሐቀኝነቱ ይራመዳል፣ ፍለጋውን የሚከተሉ ልጆቹም ደስተኞች ናቸው፡፡
ያህዌ ሆይ፣ ያለ ነቀፋ ተመላልሻለሁና አንተው ፍረደኝ፤ ያለ ማወላውል በያህዌ ተማምኛለሁ፡፡
በንግግሩ ጠማማ ከሆነና ከሞኝ ሰው ይልቅ በሃቀኝነት የሚራመድ ድሃ ሰው ይሻላል፡፡
በመንገዱ ጠማማ ከሆነ ባለጠጋ ይልቅ፣ በሐቀኝነቱ የሚራመድ ድሃ ሰው ይሻላል፡፡
ስለ ቅንነቴ እኔን ትረዳኛለህ በፊትህም ለዘላለም ታኖረኛለህ፡፡
አምልኬ ሆይ፤ ልብን እንደምትመረምርና ቅንነትን እንደምትወድ ዐውቃለሁ፤ እኔም ይህን ሁሉ የሰጠሁት በበጎ ፈቃደና በቀና መንፈስ ነው። አሁንም በዚህ ያለው ሕዝብህ በበጎ ፈቃዱ እንዴት እንደ ሰጠ አይቻለሁ።
እግዚአብሔር ትክክለኛ ያልሆነ ሚዛን ይጠላል፣ በትክክለኛ ሚዝን ግን ሚዛን ደስ ይለዋል፡፡
በነገር ሁሉ ራስህን የመልካም ሥራ ምሳሌ አድርገህ ተገኝ፤ በትምህርትም ንጽህናን፣ ጨዋነት፣ የማይነቀፍ ጤናማ ቃላት ይኑርህ።
በጥቂቱ የታመነ ሰው በብዙ ላይ የታመነ ይሆናል፤ በጥቂቱ የሚያምፅ በብዙም ዐመፀኛ ይሆናል።
ከመስዋዕት ይልቅ ጽድቅንና ፍትሕን ማድረግ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት አለው፡፡
ዳዊትም በፍጹም ቅንነት ጠበቃቸው፤ በእጁ ብልኃትም መራቸው፡፡