ስለ ቅድስና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ቅድስና የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ምክንያቱም «እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ» ተብሎ ተጽፎአል።
ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ፣ ቅድስናንም ተከታተሉ፣ ያለ ቅድስና ማንም ጌታን ሊያይ አይችልም።
እግዚአብሔር ለቅድስና እንጂ ለእርኩሰት አልጠራንም።
የተወደዳችሁ ሆይ፥ እነዚህ ተስፋዎች ስላሉን በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን እየተከተልን ስጋችንን እና መንፈሳችንን ከሚያረክስ ከማናቸውም ነገር ራሳችንን እናንፃ።
እኔ ያህዌ ቅዱስ እንደሆንኩ፣ ደግሞም ለእኔ ትሆኑ ዘንድ ከሌሎች ህዝቦች እንደለየኋችሁ ቅዱሳን ሁኑ፡፡
ስለዚህም ወንድሞች ሆይ ሥጋችሁን ህያው መስዋዕት፥ቅዱስ፥ ለእግዚአብሔር የሚገባ አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ምህረት እለምናችኋለሁ፥ ያም ተገቢ የሆነ አገልግሎታችሁ ነው።
ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ያዳነን፣ በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነው፤ ይህም የሆነው በራሱ እቅድና በጸጋወ ነው እጂ በእኛ ሥራ አይደለም፡፡
ነገር ግን የጠራችሁ እርሱ ቅዱስ እንደ ሆነ፣ እናንተም በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ፤
እግዚአብሔር በክርስቶስ የምናምነውን እኛን ዓለም ከመፈጠሩ በፊት መርጦናል። ይህም በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን እንሆን ዘንድ ነው
እኔ አምላካችሁ ያህዌ ነኝ፡፡ በምድር በሚንቀሳቀስ በማናቸውም አይነት እንስሳ ራሳችሁን አታርክሱ፡፡
አሁን ግን ከኃጢአት ነጻ ስለተደረጋችሁና ለእግዚአብሔር ባሪያዎች ስለሆናችሁ ለመቀደስ ፍሬ ታፈራላችሁ። ውጤቱም የዘላለም ሕይወት ነው።
በእርግጥ አባቶቻችን ለእነርሱ መልካም መስሎ እንደታያቸው ለጥቂት ጊዜ ይቀጡን ነበር፣ እግዚአብሔር ግን የእርሱን የቅድስናው ተካፋዮች እንድንሆን ለጥቅማችን ያቀጣናል።
በቅድስና መኖራችሁ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፣
ወደ ያህዌ ተራራ ማን ይወጣል? በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል? ንጹሕ እጅና ንጹሕ ልብ ያለው፣ ነፍሱን ለሐሰት ያላስገዛ በሐሰት የማይምል፣