ስለ በሰማይ ያለ መዝገብ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ በሰማይ ያለ መዝገብ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ብልና ዝገት በሚበላውና ሌቦችም ሰብረው በሚሰርቁበት በምድር ላይ ሀብትን ለራሳችሁ አታከማቹ፡፡ ይልቁን ብልም ሆነ ዝገት በማያጠፋበት፣ ሌቦችም ሰብረው በማይሰርቁበት በሰማይ ሀብትን ለራሳችሁ አከማቹ፡፡
ሀብታችሁ ባለበት ልባችሁም ይገኛልና፡፡
ንብረቶቻችሁን ሽጡና ለድኾች ስጡ። በማያረጅ ከረጢት ሌቦች ሊቀርቡትና ብል ሊያጠፋው የማይቻለውን የማያልቀውን ሀብት በሰማይ አከማቹ። ንብረታችሁ ባለበት ልባችሁም በዚያ ይሆናልና።
በመልካም ሥራ ባለጠጎች እንዲሆኑ፣ መልካም የሆነውን እንዲያደርጉ ለማካፈልም ፈቃደኞች እንዲሆኑ ንገራቸው፡፡ በዚህ ሁኔታ በሚመጣው ዓለም ለራሳቸው መልካም መሠረትን ይጥላሉ፣ እውነተኛውንም ሕይወት ይይዛሉ፡፡
እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ከሞት ካስነሣችሁ፤ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያሉትን ነገሮች እሹ። በላይ ስላሉት ነገሮች እንጂ በምድር ስላሉት ነገሮች አታስቡ።
! ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ይጠላል ሌላውንም ይወዳል፣ ወይም ለአንዱ ይታዘዛል ሌላውን ደግሞ ይንቃል፡፡ እግዚአብሔርንና ሀብትን ማገልገል አትችሉም፡፡
በእግዚአብሔር ፊት ባለ ጠጋ ያልሆነ ለራሱ ግን ሀብትን የሚያከማች ሰው ይህን ይመስላል።
ይህም የማይጠፋ፣ የማይበላሽ እና የማያረጅ ርስት በመንግሥተ ሰማይ ተጠብቆላችኋል።
ዓይኖቹ ወደፊት የሚቀበለውን ዋጋ አተኩረው ስለተመለከቱ፣ በግብጽ ከሚገኝ ሀብት ይልቅ ክርስቶስን መከተል የሚያስከትልበትን ውርደት የላቀ ብልጽግና አድርጎ አሰበ።
በርግጥ፥ ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ጌታዬ ዕውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቆጥራለሁ። ስለ እርሱም ሁሉን ነገር አጥቻለሁ። ክርስቶስንም ለማግኝትና በእርሱም ለመገኝት ስል ሁሉን ነገር እንደ ቤት ጥራጊ እቆጥራለሁ።
መንግሥተ ሰማይ በዕርሻ ውስጥ የተደበቀ ሀብት ትመስላለች፣ አንድ ሰውም አግኝቶ ደበቃት፤ ከደስታውም የተነሳ ያለውን ንብረት ሁሉ ሸጦ ያንን ዕርሻ ገዛው።
የሚታዩትን ነገሮች ሳይሆን የማይታዩትን ነገሮች እንመለከታለን። የምናያቸው ነገሮች ጊዜያዊ ሲሆኑ የማይታዩት ነገሮች ግን ዘላለማዊ ናቸው።
ኢየሱስም አይቶ ወደደውና አንዲት ነገር ቀርታሀለች ሂድ ያለህን ሁሉ ሽጥና ለድሆች ስጥ መዝገብም በሰማይ ይቆይሀል መጥተህም ተከተለኝ አለው፡፡