ስለ የዓለም ብርሃን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ የዓለም ብርሃን የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 ዮሐንስ 8:12
ደግሞም ኢየሱስ ሕዝቡን፣ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ ቢኖር የሕይወት ብርሃን ያገኛል እንጂ፣ በጨለማ አይመላለስም” አላቸው።
02 ዮሐንስ 1:4-5
በእርሱ ሕይወት ነበረ፤ያም ሕይወት የሰው ሁሉ ብርሃን ነበር፡፡ ብርሃኑ በጨለማ ይበራል፤ ጨለማም ሊያጠፋው አልቻለም፡፡
03 ዮሐንስ 9:5
በዓለም እስካለሁ፣ የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ።”
04 ዮሐንስ 12:46
በእኔ የሚያምን በጨለማ ውስጥ እንዳይኖር ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤
05 1ኛ ዬሐንስ 1:5
ከእርሱ የሰማነው፣ለናንተም የምንነግራችሁ መልዕክት፣ እግዚአብሔር ብርሃን ነው፤ በእርሱም ምንም ጨለማ የለም፤ የሚል ነው፡፡
06 የማቴዎስ 5:14
እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ የተመሠረተች ከተማ ልትሰወር አትችልም።
07 ኢሳይያስ 9:2
በጨለማ የሄደ ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን በራላቸው።
ጌታ፣ ‘እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ለድነት ትሆን ዘንድ፣ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ’” በማለት አዞናልና።