ስለ ቤተ ክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ቤተ ክርስቲያን የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ደግሞም አንተ ጴጥሮስ ነህም እላለሁ፤ በዚህም አለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አያሸንፏትም፡፡
ስለዚህ እናንተ አሕዛብ ከቅዱሳንና ከእግዚአብሔር ቤተ ሰብ አባላት ጋር የአንድ አገር ዜጎች ናችሁ እንጂ ከእንግዲህ መጻተኞችና እንግዶች አይደላችሁም። እነዚህ በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ የተመሠረቱ ናቸው፤ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ራሱ ነው።
እንግዲህ እናንተ የክርስቶስ አካል ስትሆኑ እያንዳንዳችሁ የአካሉ ብልቶች ናችሁ።
እነርሱም ሐዋርያት በሚያስተምሩት ትምህርትና በኅብረት፣ እንጀራውን በመቊረስና በጸሎትም ይተጉ ነበር።
እርሱ አካሉ ለሆነችው ቤተ ክርስቲያን ራስ ነው። እርሱ የሁሉም መገኛና የሁሉም የመጀመሪያ፣ከሙታንም በኩር ነው።
እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ በሕዝቡም ሁሉ ዘንድ ከበሬታ ነበራቸው። ጌታም የሚድኑትን በየቀኑ በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር።
ባሎች ሆይ፤ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ስለ እርስዋም ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ፥ እናንተም ሚስቶቻችሁን ውደዱ። ይህንንም ያደረገው በቃሉ አማካይነት በውሃ አጥቦ በማንጻት እንድትቀደስ፥ ጉድፍ ወይም የፊት መጨማደድ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ ነገር ሳይታይባት ቅድስት የሆነችና ነውር የሌለባት ክብርት ቤተ ክርስቲያን አድርጎ ለራሱ ሊያቀርባት ነው።
ነገር ግን ብዘገይ፣ በእግዚአብሔር ቤት፣ ማለትም የእውነት ዓምድና መሠረት በሆነው፣ በሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን እንዴት መኖር እንደሚገባህ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፡፡
እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ እንድታውጁ፣ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ ቅዱስ ሕዝብ፣ እግዚአብሔር የራሱ ያደረጋችሁ ሕዝብ ናችሁ። ቀድሞ የእርሱ ሕዝብ አልነበራችሁም፤ አሁን ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ ሆናችኋል፤ ቀድሞ ምሕረትን አላገኛችሁም ነበር፤ አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።
አሁን ግን፣ የሕያው እግዚአብሔር ከተማ ወደሆነችው ወደ ጽዮን ተራራ፣ አእላፋት መላእክት በደስታ ወደሚያመልኩባት ሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም መጥታችኋል፤ በሰማይ ወደሚገኙት የበኩራን ሁሉ ጉባኤ፣ የሁሉም ፈራጅ ወደሆነው እግዚአብሔርና ፍጹም የተደረጉ የጻድቃን መንፈሶች ወዳሉበት መጥታችኋል፤
ወንጌል ሰባኪዎችን፥እረኞችን እና አስተማሪዎችን ስጦታ አድርጎ የሰጠ ክርስቶስ ራሱ ነው። ያደረገው የክርስቶስን አካል ለማነጽና ለአገልግሎት ሥራ ቅዱሳንን ለማስታጠቅ ነው። የሚሆነው ሁላችንም የእግዚአብሔርን ልጅ በማመን እና በማወቅ ወደ ሚገኘው አንድነት እንዲሁም ወደ ክርስቶስ ሙላት ልክ እንዳደጉት ሰዎች ሙሉ ሰው ወደ መሆን ደረጃ እስከምንደርስ ድረስ ነው።
እንዲሁ እኛም ብዙዎች ሳለን በክርስቶስ አንድ አካል ነን እያንዳንዳችንም አንዳችን የሌላችን የአካል ክፍል ነን።
ደስ ይበለን፤ ሐሤት እናድርግ፤ የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ ሙሽራዋም ራስዋን ስላዘጋጀች፤ ደስ ይበለን፤ ሐሤት እናድርግ ፤ ክብርንም እንስጠው።”
እናንተ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደሆናችሁ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደሚኖርባችሁ አታውቁምን?
እግዚአብሔር ሁሉም ነገር በክርስቶስ እግር ሥር እንዲገዛ አድርጓል፤ እርሱንም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሁሉም ነገር ላይ ራስ አድርጎ ሾሞታል ቤተ ክርስቲያንም ሁሉንም ነገር በሁሉም መንገድ የሚሞላው የእርሱ ሙላት የሆነች አካሉ ናት።