ስለ ኅብረት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ኅብረት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
እነርሱም ሐዋርያት በሚያስተምሩት ትምህርትና በኅብረት፣ እንጀራውን በመቊረስና በጸሎትም ይተጉ ነበር።
እርሱ ብርሃን እንደሆነ ፣ በብርሃን ብንመለላለስ እርስ በርሳችን ህብረት ይኖረናል፡፡የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስም ደም ከሃጢአት ሁሉ ያነጻናል።
ለፍቅርና ለመልካም ሥራ እርስ በርስ እንዴት እንደምንነቃቃ እናስብ። አንዳንዶቹ ልማድ እንዳደረጉት በአንድነት መሰብሰባችንን አንተው። በዚህ ፈንታ ቀኑ እየቀረበ መምጣቱን ስታዩ እርስ በርሳችሁ ይበልጥ ተበረታቱ።
በየቀኑም በአንድ ዐላማ በመቅደስ እየተጉ፣ በቤት ውስጥ እንጀራ እየቈረሱም ምግብን ልባዊ በሆነ ደስታና ትሕትና ዐብረው ይመገቡ ነበር፤
በክርስቶስ መበረታታት ካላችሁ፤ከፍቅሩም መጽናናት ካላችሁ፤የመንፈስም ኅብረት ካላችሁ፤እርስ በእርሳችሁም ደግነትና ርኅራኄ ካላችሁ። ስለዚህ በአንድ አሳብ፤ በፍቅር፤ በመንፈስ አንድነት፤በአንድ ዓላማ እየተስማማችሁ ደስታዬ እንዲፈጸም አድርጉት።
ከእኛም ጋር ህብረት እንዲኖራቸሁ፣ ያየነውንና የሰማነውን እንነግራችኋለን፤ ህብረታችንም ከአብና፣ ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው፡፡
ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው።
ያመኑት ሁሉ በአንድነት ነበሩ፤ ሁሉም ነገር የጋራ ነበር፤ መሬታቸውንና ንብረታቸውን እየሸጡም ለሁሉም እንደሚያስፈልገው አካፈሉ።