ስለ አንድነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ አንድነት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

ወንድሞች ተስማምተው በአንድነት ቢኖሩ እንዴት መልካም ነው! ምንኛስ አስደሳች ነው፡፡

02 ኤፌሶን 4:3

በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ አድርጉ።

03 ፊልጵስዩስ 2:2

ስለዚህ በአንድ አሳብ፤ በፍቅር፤ በመንፈስ አንድነት፤በአንድ ዓላማ እየተስማማችሁ ደስታዬ እንዲፈጸም አድርጉት።

04 ዮሐንስ 17:21

ይህም አባት ሆይ፣ አንተ በእኔ እኔም በአንተ እንዳለሁ እነርሱም አንድ እንዲሆኑ ነው፡፡ ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ እንዲያምን እነርሱም በእኛ እንዲሆኑ እጸልያለሁ፡፡

05 ቆላስይስ 3:14

በዚህ ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነው ፍቅር ይኑራችሁ።

06 1ኛ ቆሮንቶስ 1:10

ስለዚህ ወንድሞችና እህቶች ሆይ፤ ሁላችሁም በአንድ አሳብ እንድትስማሙ እንጂ በመካከላችሁ መለያየት እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ድርስቶስ ስም አሳስባችኋለሁ። እንዲሁም በአንድ ልብና በአንድ ዓለማ የተባበራችሁ እንድትሆኑ አሳስባችኋለሁ።

07 ሮሜ 15:5-6

እንግዲህ የትዕግስትና የመጽናናት አምላክ ለእርስ በእርሳችሁ በክርስቶስ አንድ ልብ ይስጣችሁ። በአንድ ልብና በአንድ አፍ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክና አባት እንድታመስግኑ ይህን ያድርግ።

08 ኤፌሶን 4:4-6

በተጠራችሁ ጊዜ በአንድ ተስፋ እንደተጠራችሁ ሁሉ፥ አንድ አካል እና አንድ መንፈስ አለ፤ አንድ ጌታ፥አንድ እምነት፥አንድ ጥምቀት አለ ፤ ደግሞም ከሁሉ በላይ የሆነ፥በሁሉ የሚሠራ፥ በሁሉ የሚኖር ፥የሁሉም አባት የሆነ አንድ አምላክ አለ።

09 1ኛ ቆሮንቶስ 12:13

በአንድ መንፈስ በአንድ አካል እንደተጠመቅን፣አይሁድ ይሁኑ ግሪኮች፣ባሪያ ይሁን ነጻ፣ሁሉ ከአንዱ መንፈስ ጠጥተዋል።

10 ሮሜ 12:16

አንድ ልብ ይኑራችሁ፥ትሁት ሰዎችን ተቀበሉዋቸው እንጂ በትዕቢት አታስቡ። በራሳችሁ አመለካከት ጥበበኞች እንደሆናችሁ አታስቡ።

ካመኑት እጅግ ብዙዎች አንድ ልብና አንድ ነፍስ ነበራቸው፤ ከእነርሱ አንድም ሰው፣ ያለው ማንኛውም ነገር የራሱ እንደ ሆነ አልተናገረም፤ ይልቁን ሁሉም ነገሮች የጋራ ነበሩ።

12 1ኛ ጴጥሮስ 3:8

በመጨረሻም፣ ሁላችሁ በአንድ ሐሳብ ተስማሙ፤ ተዛዘኑ፤ እንደ ወንድማማቾች ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ።

13 ፊልጵስዩስ 1:27

እንግዲህ ከሁሉም በላይ ሕይወታችሁ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ይሁን፤ ይህም እኔ መጥቼ ባያችሁ ወይም ከእናንተ ብርቅ በአንድ መንፈስ ጸንታችሁ መቆማችሁንና ለወንጌልም እምነት በኅብረት መጋደላችሁን እሰማ ዘንድ ነው።

14 2ኛ ቆሮንቶስ 13:11

በመጨረሻ፣ ወንድሞችና እኅቶች፣ ደስ ይበላችሁ! ለተሐድሶ ሥሩ፤ተበረታቱ፤እርስ በርሳችሁ ተስማሙ፤በሰላም ኑሩ፤ የፍቅርና የሰላም አምልክም ከእናንተ ጋር ይሆናል።

ተዛማጅ ርዕሶች