ስለ የክርስቶስ አካል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ የክርስቶስ አካል የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 1ኛ ቆሮንቶስ 12:27

እንግዲህ እናንተ የክርስቶስ አካል ስትሆኑ እያንዳንዳችሁ የአካሉ ብልቶች ናችሁ።

02 1ኛ ቆሮንቶስ 12:12

አካል አንድ ሆኖ ሳለ ብዙ ብልቶች እንዳሉት ሁሉ፣ ሁሉም ብልቶች የእንዱ አካል ክፍል እንደሆኑ፣በክርስቶስም እንዲሁ ነው።

03 ሮሜ 12:4-5

ልክ እኛ በአንድ አካል ላይ ብዙ የአካል ክፍሎች ቢኖሩንም ተግባራቸው ግን ተመሳሳይ አይደለም። እንዲሁ እኛም ብዙዎች ሳለን በክርስቶስ አንድ አካል ነን እያንዳንዳችንም አንዳችን የሌላችን የአካል ክፍል ነን።

04 ኤፌሶን 4:15-16

ይልቁንም እውነትን በፍቅር የምንናገር እና ራስ ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ በሁሉም መንገድ የምናድግ ሰዎች መሆን ይጠበቅብናል። የአማኞችን አካል ሁሉ በሚያገናኘው ጅማት እየተያያዘና እየተጋጠመ፥እያንዳንዱም ክፍል የራሱን ተግባር እያከናወነ በፍቅር ያድጋል።

05 1ኛ ቆሮንቶስ 12:18

እግዚአብሔር ግን እያንዳንዱን የአካል ክፍል እንደወደደ ሠርቶታል።

06 1ኛ ቆሮንቶስ 12:14

አካል አንድ ብልት ብቻ ሳይሆን ብዙ ብልቶች አሉት።

አሁን ግን ብዙ ብልቶች ያሉት፣ አንድ አካል ነው። ዓይን እጅን፣"አንተ አታስፈልገኝም፣" ሊል አይችልም። ራስም እግርን፣"አታስፈልገኝም፣" ሊል አይችልም።

08 ኤፌሶን 4:16

የአማኞችን አካል ሁሉ በሚያገናኘው ጅማት እየተያያዘና እየተጋጠመ፥እያንዳንዱም ክፍል የራሱን ተግባር እያከናወነ በፍቅር ያድጋል።

09 1ኛ ቆሮንቶስ 12:25

እግዚአብሔር እንዲህ ያደረገው በአካል ውስጥ መከፋፈል እንዳይኖርና ይልቁን ብልቶች በበለጠ ፍቅር እርስ በርሳቸው አንዳቸው ሌላቸውን እንዲከባከቡ ነው።

10 ሮሜ 12:6

በተሰጠን ጸጋ በኩል ልዩ ልዩ ስጦታዎች አሉን። የአንድ ሰው ስጦታ ትንቢት መናገር ከሆነ ባመነው መጠን ያድርገው።

11 ቆላስይስ 1:18

እርሱ አካሉ ለሆነችው ቤተ ክርስቲያን ራስ ነው። እርሱ የሁሉም መገኛና የሁሉም የመጀመሪያ፣ከሙታንም በኩር ነው።

ተዛማጅ ርዕሶች