ስለ እንግዳ መቀበል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ እንግዳ መቀበል የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ቅዱሳንን በችግራቸው እርዱ፤ መልካም ለማድረግ የሚያስችላቹሁን መንገዶች ፈልጉ።
እንግዶችን መቀበል አትርሱ፣ አንዳንድ ሰዎች ይህን ሲያደርጉ ሳያውቁት መላእክትን አስተናግደዋል።
ያለ ማጒረምረም እርስ በርሳችሁ በእንግድነት ተቀባበሉ።
ነገር ግን ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ድሆችን፣ የአካል ጒዳተኞችን፣ ሽባዎችንና ዐይነ ስውራንን ጥራ፡፡ ይህን በማድረግህ እነርሱ መልሰው ሊከፍሉህ ስለማይችሉ፣ የተባረክህ ትሆናለህ፡፡ በጻድቃን ትንሣኤ ቀንም እግዚአብሔር ብድራትህን ይከፍልሃል፡፡
ስለዚህም የእውነት ማህበርተኞች እንሆን ዘንድ እንደነዚህ ያሉትን መርዳት ይገባናል።
ስለዚህ መሪው ነቀፋ የሌለበት፣ የአንዲት ሚስት ባል፣ በመጠን የሚኖር፣ አስተዋይ፣ ሥርዓት ያለው፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ለማስተማር የሚበቃ፣
ነገር ግን እንግዳ ተቀባይ፣ መልካምን የሚወድ፣ ጠንቃቃ፣ ጻድቅ፣ መንፈሳዊና ራሱን የሚገዛ መሆን አለበት።
ተርቤ ነበር ምግብ ሰጣችሁኝ፤ ተጠምቼ ነበር የምጠጣው ሰጣችሁኝ፤ እንግዳ ሆኜ ነበር አስተናገዳችሁኝ፤
ኢየሱስ ደግሞ ጋባዡን ሰው ደግሞ እንዲህ አለው፤ "የምሳ ወይም የራት ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ መልሰው ይጋብዙኛል በማለት ብድራትን በመፈለግ ወዳጆችህን ወይም ወንድሞችህን ወይም ዘመዶችህን ወይም ሀብታም ጎረቤቶችህን አትጋብዝ፡፡ ነገር ግን ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ድሆችን፣ የአካል ጒዳተኞችን፣ ሽባዎችንና ዐይነ ስውራንን ጥራ፡፡ ይህን በማድረግህ እነርሱ መልሰው ሊከፍሉህ ስለማይችሉ፣ የተባረክህ ትሆናለህ፡፡ በጻድቃን ትንሣኤ ቀንም እግዚአብሔር ብድራትህን ይከፍልሃል፡፡
ቀኑ በጣም ሞቃት በሆነ ጊዜ አብርሃም በመምሬ ወርካ ዛፎች አቅራቢይ ኣድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ እያለ ያህዌ ተገለጥለት። እርሱም ቀና ብሎ ሦስት ሰዎች ፊት ለፊቱ ቆመው አየ። ባያቸውም ጊዜ ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ፈጥኖ ወደ እነርሱ ሄዶ፣ ወደ መሬት ዝቅ ብሎም እጅ ነሣ። አብርሃም እንዲህ አለ፤ "ጌታዬ፣ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፣ ባሪያህን አልፈህ አትሂድ። ጥቂት ውሃ ትምጣላችሁና እግራችሁን ታጠቡ፤ ከዚያም ዛፉ ሥር ዐረፍ በሉ። ወደ እኔ ወዳገልጋያችሁ ከመጣችሁ የደከመ ሰውነታችሁ እንዲበረታ እስቲ ጥቂት እህል ላምጣላችሁና ብሉ፤ ከዚያ ጕዞአችሁን ትቀጥላላችሁ።" እነርሱም. "እንዳልኸው አድርግ" አሉት።
ከቤተ ሰብዋ ጋር በተጠመቀች ጊዜም፣ “በጌታ ማመኔን ከተረዳችሁልኝ ወደ ቤቴ ግቡና ተቀመጡ” ብላ ለመነችን፤ አስገደደችንም።
ፍቅር ብዙ ኀጢአትን ይሸፍናልና ከሁሉ አስቀድሞ እርስ በርሳችሁ ከልብ ተዋደዱ፤ ያለ ማጒረምረም እርስ በርሳችሁ በእንግድነት ተቀባበሉ።