ስለ ሰላም ማድረግ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ሰላም ማድረግ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 የማቴዎስ 5:9
የሚያስታርቁ የተባረኩ ናቸው፤ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።
02 ሮሜ 12:18
በተቻላችሁ መጠን በእናንተ በኩል ከሰዎች ሁሉ ጋር በሠላም ኑሩ።
03 ዕብራዊያን 12:14
ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ፣ ቅድስናንም ተከታተሉ፣ ያለ ቅድስና ማንም ጌታን ሊያይ አይችልም።
04 ቆላስይስ 3:15
የአንድ አካል ክፍሎች ሆናችሁ የተጠራችሁት ለዚህ ሰላም ስለ ሆነ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይንገሥ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ።
05 ያዕቆብ 3:18
ሰላምን ለሚያደርጉ የጽድቅ ፍሬ በሰላም ይዘራል።