ስለ ፈተና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ፈተና የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
በሰው ሁሉ ላይ ከሚደርሰው በላይ የሆነ ፈተና አልደረሰባችሁም። ነገር ግን እግዚአብሔር ታማኝ ነውና ከምትችሉት በላይ እንድትፈተኑ አያደርግም። ይልቁን ፈተናውን መወጣት እንድትችሉ ከፈተናው ጋር ማምለጫ መንገዱንም ያዘጋጅላችኋል።
02 ያዕቆብ 1:13-14
በኃጢአት ስንፈተን እግዚአብሔር እየፈተነን ነው ብለን ልናስብ አይገባም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ክፉን እንድንሠራ አይፈልግምና፤ ክፉን እንዲያደርግ ማንንም አይፈትንምና፡፡ እያንዳንዱ ሰው የሚፈተነው በራሱ ክፉ ምኞት ሲታለልና ሲሳብ ነው።
03 ዕብራዊያን 4:15
ነገር ግን እርሱ ከኃጢአት በቀር በማንኛውም ነገር እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንምና።
04 የማቴዎስ 26:41
ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፡፡ መንፈስ በእርግጥ ፈቃደኛ ነው፤ ሥጋ ግን ደካማ ነው" አለው፡፡
05 ያዕቆብ 4:7
ስለዚህ፣ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ ዲያብሎስን ተቃወሙት፤ እርሱም ከእናንተ ይሸሻል።
06 ያዕቆብ 1:12
በመከራ የሚጸኑትን ሰዎች እግዚአብሔር ያከብራቸዋል፤ ለሚወድዱት ሁሉ ተስፋ እንደ ሰጠው ለዘላለም እንዲኖሩ በማድረግ ብድራታቸውን ይከፍላቸዋል፡፡
አንተን እንዳልበድል ቃልህን በልቤ አኖራለሁ፡፡
ስለዚህ ማንም ቆሜአለሁ ብሎ የሚያስብ፣ እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።