ስለ ምቀኝነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ምቀኝነት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ያዕቆብ 3:16

ምክንያቱም ቅናትና ራስ ወዳድ ምኞት ባለበት ሁከትና ክፉ ሥራ ይኖራል።

02 ምሳሌ 14:30

በሰላም የተሞላ ልብ ለሰውነት ሕይወት ነው፣ ቅናት ግን አጥንትን ያበሰብሳል፡፡

03 ገላቲያ 5:26

አንታበይ፣ እርስ በእርሳችን ለክፉ አንነሳሳ፣ አንቀናና።

04 1ኛ ቆሮንቶስ 13:4

ፍቅር ታጋሽና ደግ ነው። ፍቅር አይመቀኝም ደግሞም አይመካም። አይታበይም

05 1ኛ ጴጥሮስ 2:1

እንግዲህ ክፋትን ፣ ማታለልን ፣ ግብዝነትን፣ ቅናትንና ሐሜትን ሁሉ አስወግዱ።

06 ቲቶ 3:3

እኛም ቀድሞ የማናስተውልና የማንታዘዝ ነበርን። የሳትንና የተለያዩ ምኞቶቻችንና ፍላጐቶቻችን ባሪያዎች ነበርን። በክፋትና በምቀኝነት እንኖር ነበር። የተጠላንና እርስበርስ የምንጠላላ ነበርን።

ክፉዎች ሲሳካላቸው ዐይቼ ቅናት አድሮብኝ ነበር፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች