ስለ ፍትወት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ፍትወት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 የማቴዎስ 5:28

እኔ ግን፣ ሴትን ተመኝቷት የሚመለከት ሁሉ በልቡ አመንዝሯል እላችኋለሁ።

02 1ኛ ዬሐንስ 2:16

በዓለም ያለው ሁሉ፣ የሥጋ ምኞት፣ የዓይን አምሮትና ትምክህት ከዓለም እንጂ ከአብ አይደሉም፡፡

03 ኢዮብ 31:1

ከዓይኔ ጋር ቃል ኪዳን ስለገባሁ፤ እንዴት ድንግሊቱን በምኞት እመለከታለሁ?

04 1ኛ ቆሮንቶስ 6:18

ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ሌላ ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚያደርግ ሰው ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ያድርጋል።

05 ገላቲያ 5:16

በመንፈስ ተመላለሱ የሥጋን ክፉ ምኞት አትፈጽሙ እላችኋለሁ።

06 1 ተሰሎንቄ 4:3-5

በቅድስና መኖራችሁ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፣ ከእናንተ እያንዳንዱ ከዝሙት በመራቅ የራሱን አካል በቅድስናና በክብር ማግኘት እንዳለበት ታውቃላችሁ፣ እግዚአብሔርን እንደማያውቁ እንደ አሕዛብ የፍትወት ምኞት አይሁን፣

07 2 ጢሞቴዎስ 2:22

ከወጣትነት ምኞት ራቅ፣ በንጹህ ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን፣ እምነትን፣ ፍቅርን፣ ሰላምን ተከታተል፡፡

08 ሮሜ 13:14

ይልቁኑ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት ለሥጋችሁና ለክፉ ምኞቱም ዕድል አትስጡ።

09 ቆላስይስ 3:5

ስለዚህ ምድራዊ ምኞቶቻችሁን ግደሉ፦ እነርሱም፦ ዝሙት፣ ርኩሰት፣ ፍትወት፣ ክፉ ምኞት፣ ስግብግብነትና ጣዖትን ማምለክ ናቸው።

10 ምሳሌ 6:25

በልብህ ውበቷን አትመኝ፣ በሽፋሽፍትዋም አትጠመድ፡፡

11 ቲቶ 2:11-12

ሰዎችን ሁሉ ሊያድን የሚችለው የእግዚአብሔር ፀጋ ተገልጧል፡፡ ይህም ፀጋ ሃጢዓተኝነትና ዓለማዊ ምኞትን እንድንክድና፣ በአሁኑ ዘመን በጥንቃቄ፣ በጽድቅና፣ እግዚአብሔርን በመምሰል እንድንኖር ያስለምደናል

12 1ኛ ጴጥሮስ 2:11

ወዳጆች ሆይ፤ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ መጠን፣ ነፍሳችሁን ከሚዋጉ ከኅጢኣት ምኞቶች እንድትርቁ እለምናችኋለሁ።

13 ሮሜ 6:12

ስለዚህ ለክፉ ምኞቱ እንድትታዘዙ በሚፈልግ የሚሞት ሥጋችሁ ላይ ኃጢአት እንዲነግሥ አትፍቀዱለት።

ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁትና በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም። ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።

ተዛማጅ ርዕሶች