ስለ ስግብግብነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ስግብግብነት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ለእነርሱም እንዲህ አላቸው፣ "ስግብግብነት ከሞላባቸው ምኞቶች ራሳችሁን ጠብቁ፣ ምክንያቱም የአንድ ሰው ሕይወት በሀብቱ ብዛት ላይ የተመሠረተ አይደለም"
የገንዘብ ፍቅር የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፡፡ አንዳንድ ሰዎች ይህን ሲመኙ ከእምነት ስተው ራሳቸውን በብዙ ሐዘን ጎዱ፡፡
አኗኗራችሁ ከገንዘብ ፍቅር የጸዳ ይሁን። እግዚአብሔር ራሱ፣ “እኔ ፈጽሞ አልተውህም፣ ደግሞም አልጥልህም” ስላለ፣ ባላችሁ ነገር ረክታችሁ ኑሩ።
! ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ይጠላል ሌላውንም ይወዳል፣ ወይም ለአንዱ ይታዘዛል ሌላውን ደግሞ ይንቃል፡፡ እግዚአብሔርንና ሀብትን ማገልገል አትችሉም፡፡
በባለጠግነታቸው ላይ የሚታመኑ ሰዎች ይወድቃሉ፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን እንደ ቅጠል ይለመልማሉ፡፡
ማንም ብርን የሚወድ በብር አይረካም፥ ማንም ብልጽግናን የሚወድ ሁልጊዜ ተጨማሪውን ይፈልጋል። ይህም ደግሞ እንፋሎት ነው።
ስግብግብ ሰው ግጭትን ያነሳሳል፣ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን ይባረካል፡፡
ባለጠጋ ለመሆን የሚመኙ በፈተና ውስጥ ይወድቃሉ፣ በወጥመድ፣ ሞኝነት በመሰሉ አያሌ ጎጂ ምኞቶች፣ እንዲሁም ሰዎችን በሚያሰጥሙና በሚያጠፉ በሌሎች ነገሮች ላይ ይወድቃሉ፡፡
ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ይተዋል፤ ሌላውን ይወዳል፤ አለበለዚያም ለአንዱ ራሱን የሰጠ ይሆናል፤ሌላውን ደግሞ ይንቃል። ስለሆነም ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።