ስለ ጣዖት አምልኮ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ጣዖት አምልኮ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 1ኛ ዬሐንስ 5:21

ልጆች ሆይ! ከጣዖታት ዓምልኮ ራሳችሁን ጠብቁ።

02 ዘጸአት 20:3-4

ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ። በላይ በሰማይ ያለውን፣ ወይም በታች በምድር ያለውን፣ ከምድርም በታች በውሀ ውስጥ ያለውን የማንኛውንም ነገር የተቀረጸ ምስልና ሥዕል ለራስህ ጣዖት አታብጅ።

03 1ኛ ቆሮንቶስ 10:14

ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ፣ከጣዖት አምልኮ ሽሹ።

04 ቆላስይስ 3:5

ስለዚህ ምድራዊ ምኞቶቻችሁን ግደሉ፦ እነርሱም፦ ዝሙት፣ ርኩሰት፣ ፍትወት፣ ክፉ ምኞት፣ ስግብግብነትና ጣዖትን ማምለክ ናቸው።

05 የማቴዎስ 6:24

! ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ይጠላል ሌላውንም ይወዳል፣ ወይም ለአንዱ ይታዘዛል ሌላውን ደግሞ ይንቃል፡፡ እግዚአብሔርንና ሀብትን ማገልገል አትችሉም፡፡

06 ዘጸአት 20:5

አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። የሚጠሉኝን ሦስትና አራት ትውልድ በልጆች ላይ ቅጣት በማምጣት የአባቶችን ኀጢአት እቀጣለሁ።

የአሕዛብ ጣዖቶች ብርና ወርቅ የሰው እጅ ሥራዎችም ናቸው፡፡ አፍ አላቸው ግን አይናገሩም ዐይን አላቸው ግን አያዩም ጆሮ አላቸው ግን አይሰሙም አፍንጫ አላቸው ግን አያሸቱም፡፡ እጅ አላቸው ግን አይዳሰስም እግር አላቸው ግን አይራመዱም ድምፅም ማሰማት አይችሉም፡፡ የሠሩአቸውና የሚታመኑባቸው ሁሉ እንደ እነዚህ ጣዖቶች ናቸው፡፡

08 ዮናስ 2:8

ልባቸውን ከንቱ አማልከት ላይ የሚያደርጉ ለእነርሱ ያለህን ጸጋ ያጣሉ፡፡

09 ኢሳይያስ 42:8

እኔ እግዚአብሔር ነኝ፣ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፣ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።

10 ሮሜ 1:25

እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት የለወጡና በፈጣሪ ፈንታ ፍጥረትን ያመለኩና ያገለገሉ ናቸው፤ እርሱ ግን ለዘላለም የተመሰገነ ነው።አሜን።

11 1ኛ ቆሮንቶስ 6:9-10

ዓመጸኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? በሐሰት አታምኑ። ዝሙት አድራጊዎች ቢሆኑ፣ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ፥ ወይም አመዝሮች ወይም ግብረ ሶዶማውዎች ቢሆኑ፤ ወይም ሌቦች፥ ወይም ስግብግቦች፤ ወይም ሰካራሞች፣ ወይም ተዳዳቢዎች፥ ወይም ነጣቂዎች፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

12 ኦሪት ዘዳግም 6:14

በዙሪያችሁ ያሉትን አሕዛብ የሚያመልኩአቸውን ሌሎችን አማልክት ፍለጋ እንዳትሄዱ፥ እንዳከተከተሉ፤

13 ገላቲያ 5:19-21

እንግዲህ የሥጋ ስራዎች የተገለጡ ናቸው። እነዚህም አስቀድሜ እንዳስጠነቀኩዋችሁ ዝሙት፣እርኩሰት፣ክፉ ምኞት፣ጣዖትን ማምለክ፣ምዋርት፣ጥል፣ክርክር፣ቅናት፣ በቁጣ መገንፈል፣አድመኛነት፣መለያየት፣ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ስካር፥ ዘፋኝነትና የመሳሰሉት ናቸው፥ ፥አስቀድሜ እንደነገርኳችሁ እነዚህን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

14 ዕንባቆም 2:18

ታዲያ፣ የቀረጽኸው ምስል ምን ይጠቅምሃል? ምስሉን የቀረጸው፣ ከቀለጠ ብረት ጣዖት የሠራ ሰው የሐሰት መምህር ነው፤ እነዚያን የማይናገሩ አማልክት ሲሠራ በገዛ እጅ ሥራው ተማምኖአልና፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች