ስለ ስንፍና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ስንፍና የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ምሳሌ 6:6

አንተ ሰነፍ ሰው፣ ወደ ጉንዳን ተመልከት፣ መንገዷን አስተውል፣ ጥበበኛም ሁን፡፡

02 ምሳሌ 13:4

ሰነፍ ሰው ይመኛል ነገር ግን አንዳችም አያገኝም፣ የትጉ ሰው ምኞት ግን በሙላት ይረካል፡፡

03 ምሳሌ 20:4

ሰነፍ ሰው በመከር ወቅት አያርስም፤ በምርት ጊዜ እህል ይለምናል ነገር ግን ምንም አያገኝም፡፡

04 ምሳሌ 24:30-31

በሰነፍ ሰው እርሻ በኩል ሄድሁ፣ አእምሮ በሌለውም ሰው የወይን እርሻ አለፍሁ፡፡ እሾህም በየቦታው በቅሎ ነበር፣ መሬቱም በሳማ ተሸፍኖ ነበር፣ የድንጋይ ካቡም ፈርሶ ነበር፡፡

05 2ኛ ተሰሎንቄ 3:10

ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ “ሊሠራ የማይወድ ማንም ቢኖር እርሱ መብላት የለበትም” ብለን አዝዘናችሁ ነበር።

06 ምሳሌ 19:15

ስንፍና ሰውን ወደ እንቅልፍ ይጥለዋል፣ ለመስራት የማይፈቅድ ግን ይራባል፡፡

07 ምሳሌ 26:14

በር በማጠፊያው ላይ እንደሚዞር፣ ሰነፍም በአልጋው ላይ ይዟዟራል፡፡

08 ምሳሌ 21:25

የሰነፍ ምኞት ራሱን ይገድለዋል፣ እጆቹ ለመስራት አይፈቅዱምና፡፡

09 መክብብ 10:18

በስንፍና ምክንያት ጣሪያ ይዘብጣል፥ በእጅ ሥራ መፍታትም ቤት ያንጠባጥባል።

ተዛማጅ ርዕሶች