ስለ እግዚአብሔር ብርሃን ነው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ እግዚአብሔር ብርሃን ነው የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 1ኛ ዬሐንስ 1:5

ከእርሱ የሰማነው፣ለናንተም የምንነግራችሁ መልዕክት፣ እግዚአብሔር ብርሃን ነው፤ በእርሱም ምንም ጨለማ የለም፤ የሚል ነው፡፡

02 ዮሐንስ 8:12

ደግሞም ኢየሱስ ሕዝቡን፣ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ ቢኖር የሕይወት ብርሃን ያገኛል እንጂ፣ በጨለማ አይመላለስም” አላቸው።

ያህዌ ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው የሚያስፈራኝ ማን ነው? ያህዌ የሕይወቴ መታመኛዋ ነው የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?

04 1ኛ ዬሐንስ 1:7

እርሱ ብርሃን እንደሆነ ፣ በብርሃን ብንመለላለስ እርስ በርሳችን ህብረት ይኖረናል፡፡የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስም ደም ከሃጢአት ሁሉ ያነጻናል።

05 ዮሐንስ 1:5

ብርሃኑ በጨለማ ይበራል፤ ጨለማም ሊያጠፋው አልቻለም፡፡

06 ያዕቆብ 1:17

ማንኛውም መልካምና ፍጹም ስጦታ እንደሚዘዋወር ጥላ ከማይለዋወጠው ከላይ ከሰማይ ከብርሃናት አባት ይወርዳል።

በአንተ ዘንድ የሕይወት ምንጭ አለ በአንተ ብርሃን ብርሃን እናያለን፡፡

08 ኢሳይያስ 60:19

ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ፣ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናልና ፀሐይ በቀን ብርሃን አይሆንልሽም፣ የጨረቃም ብርሃን በሌሊት አይበራልሽም።

ቃልህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴም ብርሃን ነው፡፡

10 ዮሐንስ 12:46

በእኔ የሚያምን በጨለማ ውስጥ እንዳይኖር ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤

11 ዳንኤል 2:22

እርሱ በጨለማ ያለውን ያውቃልና ብርሃንም ከእርሱ ጋር ነውና የጠለቁትንና የተሰወሩትን ነገሮች ይገልጣል።

የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራለት ከተማዋ የፀሐይ ወይም የጨረቃ ብርሃን አልነበራትም፤ ምክንያቱም በጉ ራሱ ብርሃንዋ ነው።

ተዛማጅ ርዕሶች