ስለ ያህዌ ይሬ (እግዚአብሔር ያዘጋጃል) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ያህዌ ይሬ (እግዚአብሔር ያዘጋጃል) የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
አብርሃምም ያን ቦታ «እግዚአብሔር ያዘጋጃል» ብሎ ጠራው። ዛሬም ቢሆን ሠዎች «እግዚአብሔር በተራራው ላይ ያዘጋጃል» ይላሉ።
ደግሞም አምላኬ እንደ ክብሩ ባለጠግነቱ በክርስቶስ ኢየሱስ አማካይነት የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሰጣችኋል።
ነገር ግን በመጀመሪያ መንግሥቱንና ጽድቁን ፈልጉ፤ ከዚያም እነዚህ ሁሉ ይጨመሩላችኋል፡፡
ያህዌ እረኛዬ ነው፤ ምንም አላጣም፡፡
አብርሃምም «ልጄ ሆይ ለመስዋዕት የሚሆነውን በግ እግዚአብሔር እራሱ ያዘጋጃል» አለው። ሁለቱም አብረው መንገዳቸውን ቀጠሉ።
አብርሃም ዙሪያውን በተመለከት ጊዜ ከበስተጀርባው ቀንዶቹ በቁጥቋጥ ዛፍ የተያዙ አንድ በግ አየ፤ አብርሃምም ሄዶ በጉን አመጣና በልጁ ፋንታ የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ አቀረበው።
እግኢአብሔር ሁልጎዜ በነገር ሁሉ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አግኝቷችሁ በብጎ ስራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።
እናንተ ቅዱሳን ያህዌን ፍሩ እርሱን የሚፈሩ አንዳች አያጡምና፡፡ አንበሶች ሊያጡ ሊራቡም ይችላሉ ያህዌን የሚሹ ግን መልካም ነገር አይጐድልባቸውም፡፡
ነገር ግን የእርሱን መንግሥት ፈልጉ፣ እነዚህም ነገሮች ይጨመሩላችኋል።
ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለሁላችን አሳልፎ የሰጠው እርሱ እንዴት ሁሉን ነገር ደግሞ ከልጁ ጋር በነጻ አይሰጠንም?
ለሚፈሩት ምግባቸውን ይሰጣል ኪዳኑንም ዘወትር ያስባል፡፡