ስለ አለት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ አለት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

ያህዌ ዐለቴ፣ መጠጊያዬና ታዳጊዬ ነው፡፡ እርሱ አምላኬ የምሸሸግበት ዐለቴ፣ ጋሻዬ፣ የድነቴ ቀንድና ዐምባዬ ነው፡፡

02 ኦሪት ዘዳግም 32:4

እርሱ ዐለትና ሥራውም ፍጹም፥ መንገዱም ሁሉ ትክክል ነው። የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፤ ቀጥተኛና ጻድቅ አምላክም እርሱ ነው።

ዐለቴና መድኃኒቴ እርሱ ብቻ ነው መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ ከቶም አልናወጥም፡፡

04 1ኛ ሳሙኤል 2:2

አንተን የሚመስልህ የለምና፥ እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለም፤ እንደ አምላካችን ያለም ዐለት የለም።

ከእግዚአብሔር በቀር ማን አምላክ አለ? ከአምላካችንስ በቀር ዐምባ ማን ነው?

06 2ኛ ሳሙኤል 22:2-3

እንዲህም እያለ ጸለየ፣ “እግዚአብሔር ዐለቴ፣ አምባዬና ታዳጊዬ ነው፡፡ እግዚአብሔር የምጠጋበት ዐለቴ፣ ጋሻዬና የድነቴ ቀንድ ነው፡፡ እርሱም ጠንካራ ምሽጌ፣ መጠጊዬና ከግፍ የሚያድነኝ ነው፡፡

07 ኢሳይያስ 26:4

ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም ዐለት ነውና ለዘላለም በእግዚአብሔር ታመኑ።

ተዛማጅ ርዕሶች