ስለ እግዚአብሔር እረኛችን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ እግዚአብሔር እረኛችን የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ያህዌ እረኛዬ ነው፤ ምንም አላጣም፡፡
መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ለበጎቹ ሲል ነፍሱን ይሰጣል።
መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፣ ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል፣ የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል።
እኔ ራሴ በጎቼን አሰማራለሁ አስመስጋቸውማለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
ያህዌ አምላክ መሆኑን ዕወቁ እርሱ ፈጠረን፤ እኛም የእርሱ ነን፡፡ እኛ ሕዝቡ የመሰማሪያውም በጐች ነን፡፡
በለመለመ መስክ ያሳድረኛል ፀጥ ባለ ውሃ ዘንድ ይመራኛል፡፡ ነፍሴን ይመልሳታል፤ ያድሳታል፡፡ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ ይመራኛል፡፡
መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ የእኔ የሆኑትን ዐውቃቸዋለው፤ የእኔ የሆኑትም ያውቁኛል።
ዮሴፍን እንደ በግ መንጋ የምትመራ፣ የእስራኤል እረኛ ሆይ፣ ስማን፡፡ በኪሩቤል ላይ ባለው ዙፋን የምትቀመጥ ሆይ፣ ብርሃንህ ይብራልን!
ቀድሞ ሁላችሁም እንደ ጠፉ በጎች ትቅበዘበዙ ነበር፤ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።
ሕዝቡን ግን እንደ በግ አሰማራቸው በምድረ በዳ እንደ መንጋ መራቸው
እርሱ አምላካችን ነውና እኛ የመሰማሪያው ሕዝብ የእጁም በጐች ነን፡፡ ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ
"ከእናንተ መካከል መቶ በጎች ያሉት ከዚያም ከእነርሱ አንዱ ቢጠፋበት ዘጠና ዘጠኙን በዱር ትቶ የጠፋበትን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልግ የማይሄድ ማንነው? ባገኘውም ጊዜ ከመደሰቱ የተነሣ በጫንቃው ይሸከመዋል።
በያህዌ ብርታት፣ በአምላኩ በያህዌ ስም ክብር ጸንቶ ይቆማል፤ መንጋውንም ይጠብቃል፡፡ በዚያ ጊዜ ታላቅነቱ እስከ ምድር ዳርቻ ስለሚደርስ ተደላድለው ይኖራሉ፡፡