ስለ እርስ በርስ መተሳሰብ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ እርስ በርስ መተሳሰብ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
እውነተኛ የወንድማማች ፍቅር ይኑራችሁ፤ እርስ በእርሳችሁ ተከባበሩ።
ስለዚህ አሁን እንደምታደርጉት ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተጽናኑ፣ አንዱም ሌላውን ያንጸው።
የእርስ በእርሳችሁን ሸክም በመሸካከም የክርስቶስን ህግ ፈጽሙ።
በራስ ወዳድነት ወይም በከንቱ ትምክህት ምንም አታድርጉ፤ነገር ግን በዚህ ፈንታ ሌሎች ሰዎች ከእናንተ እንደሚሻሉ በትህትና ቁጠሩ። እንዲሁም እያንዳንዳእሁ የራሳችሁን ጥቅም ብቻ ሳይሆን የሌላውንም ሰው ጥቅም አስቡ።
ይኽውም እርስ በርስ በፍቅር ተቻችላችሁ በፍጹም ትሕትና፥በገርነትና በትዕግሥት እንድትኖሩ ነው።
ፍቅር ብዙ ኀጢአትን ይሸፍናልና ከሁሉ አስቀድሞ እርስ በርሳችሁ ከልብ ተዋደዱ፤
እርስ በርሳችሁ ታገሱ፤ እርስ በርሳችሁም ቸሮች ሆኑ። ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅርታ ቢኖረው፣ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።
እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ዐዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ። እርስ በርሳችሁም ብትዋደዱ የእኔ ደቀ መዛሙርት እንደ ሆናችሁ ሰዎች በዚህ ያውቃሉ።»
ማንም ስለተደረገበት ክፉ ነገር ለሌላው በክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፣ ነገር ግን ለእርስ በርሳችሁና ለሰው ሁሉ መልካም የሆነውን ለማድረግ ሁልጊዜ ትጉ።
ለፍቅርና ለመልካም ሥራ እርስ በርስ እንዴት እንደምንነቃቃ እናስብ። አንዳንዶቹ ልማድ እንዳደረጉት በአንድነት መሰብሰባችንን አንተው። በዚህ ፈንታ ቀኑ እየቀረበ መምጣቱን ስታዩ እርስ በርሳችሁ ይበልጥ ተበረታቱ።
ልክ ክርስቶስ እንደተቀበላችሁ ለእግዚአብሔር ክብር እርስ በእርሳችሁ ተቀባበሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ያደረገው በአካል ውስጥ መከፋፈል እንዳይኖርና ይልቁን ብልቶች በበለጠ ፍቅር እርስ በርሳቸው አንዳቸው ሌላቸውን እንዲከባከቡ ነው።
ወንድሞች ሆይ እግዚአብሔር የጠራችሁ ለነጻነት ነው። ብቻ ነጻነታችሁን ለሥጋ ፈቃድ አትጠቀሙበት፥ በዚያ ፈንታ እርስ በእርሳችሁ በፍቅር አንዳችሁ አንዳችሁን አገልግሉ።
ወዳጆች ሆይ! እግዚአብሔር ይህን ያህል ከወደደን፣እኛም እርስ በርሳችን መዋደድ ይገባናል።