ስለ ሞት ተሸነፈ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ሞት ተሸነፈ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 2 ጢሞቴዎስ 1:10

አሁን ግን የእግዚአብሔር ማዳን፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ እና፣ ሞትን በማጥፋቱ እና የዘላለምን ሕይወት ወደ ብርሃን በማውጣቱ በወንጌሉ ተገልጦአል፣

02 1ኛ ቆሮንቶስ 15:26

ሊደመሰስ የሚገባው የመጨረሻው ጠላት ሞት ነው።

03 ዕብራዊያን 2:14-15

ስለዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ በሥጋና ደም ስለሆኑ፣ በሞቱ አማካይነት ሞት ላይ ሥልጣን ያለውን ማለትም ዲያብሎስን ለመሻር ኢየሱስም እንደ እነርሱ ሥጋ ለብሶ። ይህም የሆነው ዕድሜ ልካቸውን በሞት ፍርሃት ምክንያት ዕድሜ ልካቸውን ባርነት ውስጥ የነበሩትን ሁሉ ነጻ ለማውጣት ነው።

እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ሞት፣ ወይም ሐዘን፣ ወይም ለቅሶ ወይም ሕመም አይኖርም። ምክንያቱም የቀድሞ ነገሮች አልፈዋል።

05 ኢሳይያስ 25:8

ሞትን ለዘላለም ይውጣል፣ ጌታ እግዚአብሔርም ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፣ የሕዝቡን ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር ተናግሮአልና።

የሚጠፋው የማይጠፋውን ሲለብስ፣እና ይህ ሟች የሆነው የማይሞተውን ሲለብስ፣ እንዲህ ተብሎ የተጻፈው ይፈጸማል፣"ሞት በድል ተዋጠ።" ሞት ሆይ ድል ማድረግህ የት አለ? ሞት ሆይ መንደፊያህ የት አለ?"

07 ዮሐንስ 11:25

ኢየሱስ፣ “እኔ ትንሣኤና ሕይወት ነኝ፣ በእኔ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፡፡

08 ሮሜ 6:9

ክርስቶስ ከሙታን እንደ ተነሣና ሞቶ እንዳልቀረ እናውቃለን። ከዚህ በኋላ ሞት አይገዛውም።

09 ሮሜ 8:38-39

ሞት ቢሆን ሕይወት፥ መላእክት ቢሆኑ መንግሥታት፥አሁን ያሉት ነገሮች ወይም ሊመጡ ያሉት ቢሆኑ፥ ኃይላት ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን ዝቅታ፥ የትኛውም ሌላ ፍጥረት ቢሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየኝ እንደማይችል ተረድቻለሁ።

10 ዮሐንስ 5:24

እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማ፣ በላከኝም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ አይፈረድበትም።

እግዚአብሔር ግን ሕይወቴን ከሲኦል ኃይል ይቤዣል፤ እርሱም ይቀበለኛል፡፡ ሴላ

12 1ኛ ቆሮንቶስ 15:57

ነገር ግን በጌታ በክርስቶስ ኢየሱስ ድል የሚሰጠን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!

ሞትና ሲኦል ወደ እሳቱ ባሕር ተጣሉ። የእሳቱም ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው።

14 ዮሐንስ 8:51

እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚጠብቅ ማንም ቢኖር፣ እርሱ ሞትን በፍጹም አያይም።”

15 ሆሴዕ 13:14

በእርግጥ ከሲዖል ኃይል አድናቸዋለሁን? በእርግጥ ከሞትስ አድናቸዋለሁን? ሞት ሆይ መቅሰፍቶችህ ወዴት አሉ? ወደዚህ አምጣቸው። ሲዖል ሆይ ማጥፋትህ ወዴት አለ? ወደዚህ አምጣው። ርህራኄ ከዓይኖቼ ተሰወረ።

ተዛማጅ ርዕሶች