ስለ ባዶው መቃብር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ባዶው መቃብር የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ሉቃስ 24:6

እርሱ በዚህ የለም፣ ተነሥቷል! ገና በገሊላ ሳለ፣

02 የማቴዎስ 28:6

እንደ ተናገረ ተነሥቷል እንጂ፣ እዚህ የለም፤ ኑና የነበረበትን ቦታ እዩ።

03 ማርቆስ 16:6

እርሱም አትገረሙ፣ የምትፈልጉት ተሰቅሎ የነበረውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ነው፡፡ ያኖሩበትን ቦታ ተመልከቱ፤ እርሱ በዚህ የለም፣ ተነሥቷል፡፡

04 ዮሐንስ 20:6-7

ከእርሱም በኋላ ጴጥሮስ ደረሰና ወደ መቃብሩ ውስጥ ገባ። የበፍታ ጨርቁ ተቀምጦ አየ፣ በኢየሱስ ራስ ላይ የነበረውንም ጨርቅ ከበፍታ ጨርቁ ጋር ዐብሮ ሳይሆን ለብቻው እንደ ተጠቀለለ በቦታው ተቀምጦ አየ።

05 1ኛ ቆሮንቶስ 15:4

ተቀበረ፣ በሦስተኛውም ቀን ተነሳ፣መጽሐፍትም ይህን ያረጋግጣሉ።

ተዛማጅ ርዕሶች