ስለ በኵራት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ በኵራት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ግን እያንዳንዱ በቅደም ተከተሉ መሠረት፦ ክርስቶስ በኩር፣ ቀጥሎ የክርስቶስ የሆኑት እርሱ ተመልሶ ሲመጣ ሕያዋን ይሆናሉ።
አሁን ግን ክርስቶስ ከሙታን ሁሉ በኩር ሆኖ ተነስቷል።
ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ውስጥ ቢኖር ክርስቶስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በውስጣችሁ በሚኖረው በቅዱስ መንፈሱ አማካይነት ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል።
እርሱ አካሉ ለሆነችው ቤተ ክርስቲያን ራስ ነው። እርሱ የሁሉም መገኛና የሁሉም የመጀመሪያ፣ከሙታንም በኩር ነው።
ኢየሱስ እንደሞተና እንደተነሳ ካመንን በእርሱ አምነው ያንቀላፉትን እግዚአብሔር ከኢየሱስ ጋር ያመጣቸዋል።
በአዳም ሁሉም እንደሞቱ፣ሁሉም ደግሞ በክርስቶስ ሕያው ይሆናሉ።
ይኸውም ክርስቶስ መከራ ይቀበላል፤ ከሙታን ለመነሣትና ለአይሁድ ሕዝብ፣ ለአሕዛብም ብርሃንን ለመስበክ የመጀመሪያው ይሆናል የሚል ነው።
እንዲሁም ታማኝ ምስክር፥ከሙታን በኩርና የምድር ነገሥታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለሚወደንና ከኀጢአታችንም በደሙ ነጻ ላወጣን፥
በፍጥረታቱ መካከል እንደ በኵራት እንድንሆን እግዚአብሔር በእውነት ቃል ሕይወት ሊሰጠን ወደደ።
ይህም ብቻ አይደለም፥ነገር ግን የመንፈስ ቅዱስ የመጀመሪያው ፍሬ ያለን እኛ፥የሰውነታችን ቤዛ የሚሆነውን ልጅነታችንን እየተጠባበቅን እኛ ራሳችን እንኳን በውስጣችን እንቃትታለን።
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ ይባረክ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት በመነሣቱ ምክንያት ላገኘነው ርስት ዋስትና እንዲሆነን በታላቅ ምሕረቱ አዲስ ልደትን ሰጠን፤
እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ የስንዴ ዘር ወደ ምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ከሞተች ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች፡፡” ብሎ መለሰላቸው፡፡
ሞት በአንድ ሰው በኩል እንደመጣ፣ የሙታን ትንሣኤም በአንድ ሰው በኩል መጥቷል።
ልጁ የማይታየው አምላክ ምሳሌ ነው። እርሱ የፍጥረት ሁሉ በኩር ነው።
ሕያውም ሆኜ የምኖር ነኝ። ሞቼ ነበር፤እነሆም ለዘላለም ሕያው ነኝ፤የሞትና የሲዖል መክፈቻም አለኝ።