ስለ የትንሣኤው ኃይል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ የትንሣኤው ኃይል የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ይኸውም እርሱን የማወቅ ጽድቅ፤ የእርሱ የትንሣኤ ኃይልና የመከራው ተካፋይ የመሆንና በሞቱም ክርስቶስን ለመምሰል ነው።
እንዲሁም እንደ ኀይሉ ብርታት አሠራር በእኛ በምናምነው ውስጥ የሚሠራው የኀይሉ ታላቅነት ምን እንደሆነ እንድትረዱ ነው። ይህም እግዚአብሔር ከሙታን ባስነሳውና በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ እንዲቀመጥ ባደረገው ጊዜ በክርስቶስ ውስጥ የታየው ኀይል ነው።
እንግዲህ ከሞቱ ጋር ለመተባበር በጥምቀት አማካይነት ከእርሱ ጋር ተቀብረናል። ይህም የሆነው ልክ ክርስቶስ በአብ ኃይል ከሙታን እንደ ተነሣ እኛ ደግሞ በታደሰ ሕይወት እንድንመላለስ ነው።
ጌታ ኢየሱስን ከሞት ያስነሳው እኛንም ከእርሱ ጋር ያስነሳናል። ከእናንተም ጋር ወደ ፊቱ እንዲያመጣን እናውቃለን።
ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ። ከእንግዲህ የምኖረው እኔ አይደለሁም፥ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል። አሁን በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና እራሱን ስለ እኔ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።
ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ውስጥ ቢኖር ክርስቶስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በውስጣችሁ በሚኖረው በቅዱስ መንፈሱ አማካይነት ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል።
እግዚአብሔርም ደግሞ ጌታን አስነሣ እኛንም በኃይሉ ያስነሣናል።ሥጋችሁ የክርስቶስ ብልቶች እንደሆነ አታውቁምን?