ስለ ኑዛዜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ኑዛዜ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
በዚያን ጊዜ ኃጢአቴን ለአንተ ተናዘዝሁ በደሌንም ከአንተ አልሰወርሁም ደግሞም፣ «መተላለፌን ለያህዌ እናዘዛለሁ» አልሁ አንተም የኃጢአቴን በደል ይቅር አልህ፡፡ ሴላ
ነገር ግን ሃጢያታችንን ብንናዘዝ፣ሃጢያታችንን ይቅር ሊለንና ከዓመጽ ሁሉ ሊያነጻን፣ የታመነና ፃድቅ ነው፡፡
ኃጢአቱን የሚሸሽግ አይሳካለትም፣ የሚናዘዝና የሚተወው ግን ምህረትን ያገኛል፡፡
እንዲሁ ጌታ ከበሽታ ሊፈውስና ኃጢአትን ይቅር ሊል ስለሚችል ያደረጋችሁትን ኃጢአት በተመለከተ አንዳችሁ ለሌላችሁ ተናዘዙ፡፡ ጻድቃን ሰዎች ከጸለዩና አንድ ነገር እንዲያደርግላቸው ጌታን አጥብቀው ከጠየቁት፣ እግዚአብሔር ይገለጣል፤ ደግሞም በእርግጠኝነት ያን ነገር ያደርገዋል፡፡
በደሌን እናዘዛለሁ ኃጢአቴም አስጨንቆኛል፡፡
ስለዚህም ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህ። ምክንያቱም ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃል በአፉ መስክሮ ደግሞ ይድናል።
ሃጢያት የለብንም ብንል፣ ራሳችንን እናስታለን፣ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
የኑዛዜ ቃላት ያዝና ወደ እግዚአብሔር ተመለስ። እንዲህም በሉት፦«የከንፈሮቻችንን ፍሬ ምስጋናችንን እንሰዋልህ ዘንድ፤ክፋታችንን አስወግድ፥በቸርነትም ተቀበለን።
እኛ ኃጢአት ሠርተናል፣ በድለናልም፣ ክፋትን አድርገናል፣ ዐምፀናልም፣ ከትእዛዝህና ከሕግህ ዘወር ብለናል።