ስለ ንጹሕ ልብ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ንጹሕ ልብ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

አምላኬ ሆይ፣ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ ቀና የሆነውንም መንፈስ በውስጤ አድስ

በሂሶጵ እርጨኝ እኔም እነጻለሁ፡፡ እጠበኝ፤ ከበረዶም ይልቅ እነጻለሁ፡፡

03 የማቴዎስ 5:8

ልበ ንጹሖች የተባረኩ ናቸው እግዚአብሔርን ያዩታልና።

04 ሕዝቅኤል 36:26

አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ።

05 ዕብራዊያን 10:22

ልባችን በመረጨት ከክፉ ኅሊና ሁሉ ነጽቶ፣ ሥጋችንም በንጹሕ ውኃ ታጥቦ ባገኘነው የእምነት ሙሉ ዋስትና በእውነተኛ ልብ እንቅረብ።

06 ኤርሚያስ 17:9

ልብ ከየትኛውም ነገር ይልቅ ተንኰለኛ ነው። በሽተኛ ነው፤ ማንስ ያስተውለዋል?

07 ያዕቆብ 4:8

ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፣ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች እጆቻችሁን አንጹ፤ እናንተ በሁለት ሐሳብ የምትዋልሉ ልባችሁን አጥሩ።

08 1 ጢሞቴዎስ 1:5

ነገር ግን የትእዛዙ ግብ ከንጹህ ልብ፣ ከመልካም ኅሊና እና ከእውነተኛ እምነት የሚወጣ ፍቅር ነ

09 ሕዝቅኤል 11:19

ወደኔ ሲቀርቡ አንድ ልብ እሰጣቸዋለሁ፥ በውስጣቸውም አዲስ መንፈስ አስቀምጣለሁ፤

ተዛማጅ ርዕሶች