ስለ መንጻት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ መንጻት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ኢሳይያስ 1:18

"አሁን ኑና በአንድ ላይ እንዋቀስ" ይላል እግዚአብሔር፤ "ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን፣ እንደ በረዶ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ፣ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።

02 1ኛ ዬሐንስ 1:7

እርሱ ብርሃን እንደሆነ ፣ በብርሃን ብንመለላለስ እርስ በርሳችን ህብረት ይኖረናል፡፡የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስም ደም ከሃጢአት ሁሉ ያነጻናል።

በሂሶጵ እርጨኝ እኔም እነጻለሁ፡፡ እጠበኝ፤ ከበረዶም ይልቅ እነጻለሁ፡፡

04 ሕዝቅኤል 36:25

ከእርኩሰታችሁ ሁሉ እንድትነጹም ጥሩ ውኃን እረጭባችኋለሁ። ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አጠራችኋለሁ።

05 ዕብራዊያን 9:14

ይልቁንም ነውር ሳይኖረው በዘላለማዊ መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እናገለግል ዘንድ ሕሊናችንን ከሞተ ሥራ ምን ያህል ያነጻን ይሆን?

06 ቲቶ 2:14

ኢየሱስ ራሱን ለእኛ የሰጠው፣ ከዓመፅ ነፃ ሊያወጣንና ሊያነፃን፣ ገንዘቡና መልካምን ለማድረግ የሚናፍቅ ሕዝብ፣ ለራሱ ሊያደርገን፣ ዋጋ ለመክፈል ነው።

07 1ኛ ቆሮንቶስ 6:11

ከእናንተም አንዳንዶቻችሁ እንዲሁ ነበራችሁ። ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፤ ጸድቃችሁማል።

በደሌን ፈጽሞ እጠብልኝ ከኃጢአቴም አንጻኝ፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች