ስለ ንስሐ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ንስሐ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

እንግዲህ ኀጢአታችሁ እንዲደመሰስ፣ ከጌታ ዘንድም የመታደስ ዘመን እንዲመጣ ንስሓ ግቡ፤ ተመለሱም፤

02 ማርቆስ 1:15

ተፈጸመ፤የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንሰሐ ግቡ፤ በወንጌልም እመኑ ይል ነበር፡፡

03 ሉቃስ 13:3

አይደለም፤ እናንተም ንስሓ ካልገባችሁ እንዲሁ ትጠፋላችሁ ።

04 2ኛ ጴጥሮስ 3:9

አንዳንድ ሰዎች የዘገየ እንደሚመስላቸው ጌታ የተስፋ ቃሉን ለመፈጸም አይዘገይም፤ ነገር ግን ከእናንተ መካከል አንዳችሁም እንድትጠፉ ስለማይፈልግና ሰው ሁሉ በቂ የንስሓ ጊዜ እንዲያገኝ ፈልጎ ስለ እናንተ ይታገሳል።

ስለዚህ እግዚአብሔር የአለማወቅ ጊዜያትን አሳልፎ፣ አሁን ግን በየትኛውም ስፍራ ያሉ ሰዎች ሁሉ ንስሐ እንዲገቡ ያዛል።

ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፤ “ንስሓ ግቡ፤ እያንዳንዳችሁም ለኀጢአታችሁ ይቅርታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ መንፈስ ቅዱስንም በስጦታነት ትቀበላላችሁ።

07 ሉቃስ 15:7

እንዲሁም ንስሓ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሓ በሚገባ በአንድ ኅጢአተኛ በሰማይ ታላቅ ደስታ እንደሚሆን እነግራችኋለሁ።

08 ሁለተኛ ዜና 7:14

በስሜ የተጠሩት ህዝቤ ራሳቸውን ቢያዋርዱ፥ ቢጸልዩ፥ ፊቴን ቢፈልጉና ከክፉ መንገዳቸው ቢመለሱ ከሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፤ ኃጢአታቸውን ይቅር እላለሁ፤ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ፡፡

09 ሕዝቅኤል 18:30

የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ስለዚህ በመካከላችሁ በእያንዳንዱ ሰው እንደ መንገዱ እፈርድበታለሁ! ይላል ጌታ እግዚአብሔር። ንስሐ ግቡ ኃጢአትም ዕንቅፋት እንዳይሆንባችሁ ከኃጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።

10 የማቴዎስ 4:17

ኢየሱስ ከዚያ ጊዜ አንሥቶ፣ ‹‹መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ›› እያለ መስበክ ጀመረ፡፡

ነገር ግን መጀመሪያ በደማስቆ ላሉት፣ ከዚያም በኢየሩሳሌም፣ በመላው ይሁዳ፣ ደግሞም ለአሕዛብ ንስሓ እንዲገቡ፣ ወደ እግዚአብሔር ዘወር እንዲሉና ለንስሓ የሚገባ ሥራ እንዲሠሩ ሰበክሁ።

ተዛማጅ ርዕሶች