ስለ የኃጢአት ስርየት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ የኃጢአት ስርየት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 1ኛ ዬሐንስ 1:9

ነገር ግን ሃጢያታችንን ብንናዘዝ፣ሃጢያታችንን ይቅር ሊለንና ከዓመጽ ሁሉ ሊያነጻን፣ የታመነና ፃድቅ ነው፡፡

02 ኤፌሶን 1:7

እንደ ጸጋው ባለጠግነት መጠን በሚወደው ልጁ ደም ቤዛነትን ይኸውም የሐጢአት ይቅርታን አገኘን።

03 ቆላስይስ 1:14

በልጁም የኅጢአታችንን ይቅርታ፣ ድነትን አገኘን።

በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኀጢአትን ይቅርታ እንዲቀበል ነቢያት ሁሉ የሚመሰክሩት ስለ እርሱ ነው።”

ኃጢአትን ይቅር የሚል የርስቱንም ትሩፍ መተላለፍ የሚምር እንደ አንተ ያለ አምላክ ማነው? የኪዳን ታማኝነትህን ለእኛ ማሳየት ደስ ስለሚልህ አንተ ለዘላለም አትቆጣም፡፡ እንደ ገና ትራራልናለህ፤ ርኩሰታችንን በእግሮችህ ትረግጣለህ፡፡ ኃጢአታችንን ሁሉ ወደ ባሕሩ ጥልቅ ትጥላለህ፡፡

ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ በደልና ኃጢአታችንን በዚያው መጠን ከእኛ አስወገደ፡፡

07 ኢሳይያስ 1:18

"አሁን ኑና በአንድ ላይ እንዋቀስ" ይላል እግዚአብሔር፤ "ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን፣ እንደ በረዶ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ፣ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።

08 ቆላስይስ 2:13-14

እናንተም በበደላችሁና በሥጋችሁ ባለመገረዝ ሙታን ሳላችሁ፤ እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ሕያዋን አድርጎ መተላለፋችንንም ሁሉ ይቅር ብሎአል። እርሱ ይከሰን የነበረውን የዕዳ ጽሑፍ ደመሰሰው። ሁሉንም በመስቀል ላይ ቸንክሮ ከእኛ አስወገደው።

09 ዕብራዊያን 8:12

በዓመፅ ለፈጸሟቸው ድርጊቶች ሁሉ ምሕረት አደርጋለሁና ኃጢአቶቻቸውንም ከእንግዲህ አላስብምና”

10 ሮሜ 4:7-8

እርሱም፤ "መተላለፋቸው የተተወላቸው፥ ኃጢአታቸውም የተከደነላቸው እነርሱ የተባረኩ ናቸው። ጌታ ኃጢአቱን የማይቆጥርበት ያ ሰው የተባረከ ነው።" ብሏል።

11 ሉቃስ 24:47

ደግሞም ንስሐና የኃጢአት ይቅርታ ከኢየሩሳሌም ጀምሮ ለአሕዛብ ሁሉ በስሙ መሰበክ አለበት።

መተላለፉ ይቅር የተባለለት ኃጢአቱም የተሸፈነለት ሰው ቡሩክ ነው፡፡

13 የማቴዎስ 26:28

ይህ ለብዙዎች ኀጢአት ይቅርታ የሚፈስ የኪዳኑ ደሜ ነው፡፡

14 ዕብራዊያን 10:17-18

ቀጥሎም፣ “ኃጢአታቸውንና ዓመጻቸውን ከእንግዲህ አላስበውም” አለ። ለእነዚህ ነገሮች ይቅርታ በተረገበት በዚያ ለኃጢአት ከእንግዲህ ወዲያ መሥዋዕት አይቀርብም።

ተዛማጅ ርዕሶች