ስለ ምስክርነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ምስክርነት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ ሲመጣ፣ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፣ በሰማርያና እስከ ምድር ዳርቻ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።”
እኛ ስላየናቸውና ስለ ሰማናቸው ነገሮች ለመናገር ዝም ማለት አንችልም።”
ይልቁንም፣ ክርስቶስ የከበረ መሆኑን ተረድታችሁ በልባችሁ ቀድሱት። እናንተ በእግዚአብሔር ላይ ስላላችሁ መታመን ምክንያቱን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁል ጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን ይህን ሁሉ በትሕትናና በአክብሮት አድርጉት፤
ከመጀመሪያ ጀምሮ ከእኔ ጋር ስለ ነበራችሁ፣ እናንተም ትመሰክራላችሁ።
መልካሙን ሥራችሁን እንዲያዩና በሰማይ ያለ አባታችሁን እንዲያከብሩት መብራታችሁ እንዲሁ በሰዎች ፊት ይብራ።
ስለዚህም ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህ። ምክንያቱም ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃል በአፉ መስክሮ ደግሞ ይድናል።
ናትናኤል፣ «ከናዝሬት መልካም ነገር ይወጣልን?» አለው፡፡ ፊልጶስም መጥተህ እይ አለው፡፡
ምክንያቱም ስለ አየኸውና ስለ ሰማኸው ነገር ለሰዎች ሁሉ ምስክር ትሆንለታለህ።
እናንት እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሁሉ ኑና ስሙ፣ ለነፍሴ ያደረገላትን እነግራችኃለሁ፡፡
ሰውየውም፣ “እኔ እርሱ ኀጢአተኛ መሆኑን አላውቅም። ነገር ግን አንድ ነገር ዐውቃለሁ፤ ዐይነ ስውር ነበርሁ፤ አሁን ግን እያየሁ ነው” አላቸው።
አልፈቀደለትም፤ ይልቁንም ወደ ቤትህ፣ ወደ ዘመዶችህ ሂድ፣ ጌታ ለአንተ እንዴት ታላላቅ ነገሮችን እንዳደረገልህ፣ እንዴትም ምሕረቱን ባንተ ላይ እንዳሳየ ንገራቸው አለው፡፡