ስለ ታላቁ ተልእኮ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ታላቁ ተልእኮ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ስለዚህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ፣ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስም ስም እያጠመቃችኋቸው፤ እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ እንዲያደርጉ እያስተማራችኋቸው፤ ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው። እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ ሲመጣ፣ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፣ በሰማርያና እስከ ምድር ዳርቻ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።”
እንዲህም አላቸው፣ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፣ ወንጌልንም ለፍጥረት በሙሉ ስበኩ አላቸው፡፡
ደግሞም ንስሐና የኃጢአት ይቅርታ ከኢየሩሳሌም ጀምሮ ለአሕዛብ ሁሉ በስሙ መሰበክ አለበት።
እንደ ገናም ኢየሱስ፣ «ሰላም ለእናንተ ይሁን፣ አብ እንደ ላከኝ እኔም እልካችኋለሁ» አላቸው።
ኢየሱስ ወደ እነርሱ መጥቶ፣ “በሰማይና በምድር ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠኝ።
ከብዙ ምስክሮች ጋር ከእኔ የሰማኸውን፣ ሌሎችን ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ፡፡
ታዲያ ያላመኑበትን እንዴት ይጠሩታል? ስለእርሱ ሳይሰሙስ እንዴት ያምኑበታል? ያለ ሰባኪስ ከየት ይሰማሉ? «በመልካም ነገር የተሞላ ደስታን የሚሰብኩ እግሮች እንዴት ያማሩ ናቸው» ተብሎ እንድተጻፈ፣ ሳይላኩስ እንዴት ይሰብካሉ?
ያመነና የተጠመቀም ይድናል፣ ያላመነ ግን ይፈረድበታል፡፡
እነርሱም፣ “እናንተ የገሊላ ሰዎች፣ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ለምን እዚህ ትቆማላችሁ? ወደ ሰማይ የወጣው ይህ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ ባያችሁበት ሁኔታ ተመልሶ ይመጣል” አሏቸው።
ስለዚህም እግዚአብሔር በእኛ ሆኖ ልመናውን እንደሚያቀርብ፥ የክርስቶስ ተወካዮች ሆነን ተሹመናል። ከእናንተም ጋር በመሆን ስለ ክርስቶስ "ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ!" ብለን ልመና እናቀርባለን።
የጌታንም ድምፅ፣ "ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል?" ሲል ሰማሁ። እኔም፣ "እኔ አለሁ፤ እኔን ላከኝ።" አልሁ።