ስለ ድፍረት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ድፍረት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ጌታ ሆይ፣ አሁን ወደ ዛቻዎቻቸው ተመልከት፤ ለባሪያዎችህም ቃልህን በሙሉ ድፍረት እንዲናገሩ ስጥ።
ጸሎት ሲጨርሱ፣ ተሰብስበውበት የነበረው ስፍራ ተናወጠ፤ ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ፤ የእግዚአብሔርን ቃልም በድፍረት ተናገሩ።
ኃጢአተኛ ማንም ሳያባርረው ይሸሻል፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን እንደ አንበሳ ደፋር ናቸው፡፡
እግዚአብሔር የኃይል እና የፍቅር ራስንም የመግዛት እንጂ፣ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንም፡፡
ምስጢር በድፍረት ለመናገር አፌን በምከፍትበት ጊዜ ሁሉ ቃል ይሰጠኝ ዘንድ ለእኔም ጸልዩልኝ። መናገር እንደሚገባኝ በድፍረት እናገር ዘንድ በሰንሰለት የታሰረ መልእክተኛ የሆንሁት ለዚሁ ነውና።
የጴጥሮስንና የዮሐንስን ድፍረት ሲያዩ፣ ያልተማሩና ተራ ሰዎች እንደ ሆኑ ሲያውቁም፣ ጴጥሮስና ዮሐንስ ከኢየሱስ ጋር እንደ ነበሩ በማወቅ ተደነቁ።
እንደማላፍርበት በሙሉ መተማመ እጠባበቃለሁ። ነገር ግን ዘወትር እንደማደርገውና በተለይም ዛሬም በሕይወት ብኖር ወይም ብሞት ክርስቶስ በሰውነቴ ይከብራል ብዬ በድፍረት እናገራለሁ።
ይሁን እንጂ፣ በርናባስ ወስዶ ወደ ደቀ መዛሙርቱ አቀረበው። ሳውል ጌታን በመንገድ ላይ እንዴት እንዳየው፣ ጌታም እንደ ተናገረው፣ በኢየሱስ ስም ደማስቆ ውስጥ በድፍረት እንዴት እንደ ሰበከም ነገራቸው። ሳውል ኢየሩሳሌም ውስጥ ሲገባና ከዚያም ሲወጣ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተገናኘ። በጌታ ኢየሱስ ስም በድፍረት ተናገረ፤
የእግዚአብሔርን መንግሥት ይሰብክ፣ ያስተምርም ነበር። ይህንም ሲያደርግ ማንም አልከለከለውም።
ስለዚህ በሚያስፈልገን ጊዜ ምሕረትንና የሚረዳንን ጸጋ እንድንቀበል ወደ ጸጋው ዙፋን በድፍረት እንቅረብ።
በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና፦ "ጽና፥ አይዞህ፥ አትፍራ፥ ተስፋ አትቁረጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?"
በክርስቶስ በማመናችን በእርሱ ሆነን በድፍረትና በልበ ሙሉነት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንችላለንና።
ጳውሎስና በርናባስም በጌታ ኀይል በድፍረት እየተናገሩ ረዘም ላለ ጊዜ በዚያ ተቀመጡ፤ ጌታም ስለ ጸጋው የሚነገረውን መልእክት በማስረጃ ለመደገፍ ጳውሎስና በርናባስ ምልክትና ድንቅ በእጃቸው እንዲደረግ ሰጠ።