ስለ ከነገድና ከቋንቋ ሁሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ከነገድና ከቋንቋ ሁሉ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ከዚህ በኋላ ከሕዝብ፥ከነገድ፥ከወገንና ከቋንቋ ሁሉ የመጡ ቁጥራቸው ማንም ሊቆጥረው የማይችል አጅግ ብዙ ሕዝብ ነጭ ልብስ ለብሰው፥ በእጃቸውም የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆመው አየሁ።
እነርሱም እንዲህ የሚል አዲስ ቅኔ ዘመሩ፤«መጽሓፉን ትወስድ እና ማኅተሞቹን ተፈታ ዘንድ ይገባሃል፤ ታርደሃልና በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ፥ከቋንቋ ሁሉ፥ ከሕዝብና ከአገር ሁሉ ሰዎችን ዋጅተሃል።
የምድር ሕዝቦች ሁሉ ያስታውሳሉ ወደ ያህዌም ይመለሳሉ፤ የምድር ወገኖች ሁሉ በፊትህ ወድቀው ይሰግዳሉ፡፡
በዚህም ምክንያት ጉልበት ሁሉ በሰማይና በምድር፤ ከምድርም በታች ሁሉ በኢየሱስ እግሮች በታች እንዲንበረከኩ ነው። አንደበትም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር እንዲሆን፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ ነው ብሎ እንዲመሰክር ነው።
ሥልጣን፣ ክብርና ታላቅ ኃይል ተሰጠው፤ በልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች፤ መንግሥታትና ሕዝቦች ሰገዱለት፤ ግዛቱም ለዘላለም የማያልፍ ነው፤ መንግሥቱም ፈጽሞ የማይጠፋ ነው።
በሰማይና በምድር፥ከምድር በታች እንዲሁም በባሕር ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ ፥«ምስጋና፥ክብር፥ውዳሴ፥የመግዛትም ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው እና ለበጉ ይሁን።» ሲሉ ሰማሁ፤
'ቃሌ ከአፌ በጽድቅ ወጥታለች፣ አትመለስም። ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፣ ምላስም ሁሉ በእኔ ይምላል ብዬ በራሴ ምያለሁ።
ምክንያቱም «እኔ ህያው ነኝና ጉልበት ሁሉ በፊቴ ይንበረከካል ምላስም ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናል» ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፏል።
የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል በእነዚያ ቀኖች ከየወገኑና ከየቋንቋው አሥር ሰዎች የእናንተን ልብስ ዘርፍ አጥብቀው በመያዝ፣ “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና፤ ከእናንተ ጋር እንሂድ! ይላሉ።