ስለ በሙሉ ልብ መሰጠት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ በሙሉ ልብ መሰጠት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ "እግዚአብሔር አምላክህን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህና በሙሉ ዐሳብህ ውደድ፡፡"
እናንተም እግዚአብሔር አምላካችሁን በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁ፥ በፍጹም ኃይላችሁ ውደዱ።
እግዚአብሔርንም ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ፥ እባቶቻችሁ በኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ሳሉ ያመለኩአቸውን አማልክት ወይም በምድራቸው ያላችሁባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ፥ የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤተ ሰቦቼ ግን እግዚአብሔርን እናመካለን።
በሙሉ ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፣ በራስህም ማስተዋል ላይ አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፣ እርሱም መንገድህን ቀና ያደርገዋል፡፡
የምታደርጉትን ሁሉ ለሰው እንደምታደርጉ ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ በሙሉ ልባችሁ አድርጉት።
አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህ፣በፍጹም አሳብህ፣ በፍጹምም ኀይልህ ውደድ የምትለዋ ናት፡፡
ያህዌ ሆይ፣ መንገድህን አስተምረን፤ እኔም በእውነትህ እሄዳለሁ፡፡ ባልተከፋፈለ ልብም እንዳከብርህ አድርገኝ፡፡
ስለዚህም በዛሬው ቀን በድንጋጌው ለመመላለስና ትእዛዞቹንም ታከብሩ ዘንድ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ለአምላካችን በልባችሁ ታማኞች ሁኑ፡፡
ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የተሰጠ የሆነውን ሰው በኃይሉ ያበረታ ዘንድ የእግዚአብሔር ዓይኖች በምድር ሁሉ ላይ ይዘዋወራሉ፡፡ ነገር ግን አንተ በዚህ ጉዳይ ስንፍና አድርገሃል፡፡ ከአሁን ጊዜ ጀምሮ ጦርነት ይሆንብሃል" አለው፡፡