ስለ መታዘዝ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ መታዘዝ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
የምትወዱኝ ከሆነ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ።
ሳሙኤልም፥ "የእግዚአብሔርን ድምፅ ከመታዘዝ የበለጠ በሚቃጠል መባና መሥዋዕት እግዚአብሔር ደስ ይሰኛል? ከመሥዋዕት መታዘዝ ይሻላል፥ ከአውራ በግ ስብም መስማት ይሻላል።
ለቃሉ ታዘዙ እንጂ፣ ሰሚዎች ብቻ በመሆን ራሳችሁን አታታልሉ።
ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ «ማንም ሰው ቢወደኝ ቃሌን ይጠብቃል። አባቴም ይወደዋል፣ ወደ እርሱ እንመጣለን፣ መኖሪያችንንም በእርሱ እናደርጋለን።
እግዚአብሔርን የምንወደው የርሱን ትእዛዙን በመጠበቃችን ነው። የርሱም ትእዛዛት ከባዶች አይደሉም።
ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁን ውዳዱት፥ ሁልጊዜም መመሪያዎቹን፥ ሥርዓቶቹን፥ ድንጋጌዎችንና ትእዛዛትን ጠብቁ።
ስለዚህ ሕግ መጽሐፍ ሁልጊዜ ተናገር። የተጻፈበትንም ሁሉ ትጠብቅ ዘንድ በቀንና በሌሊትም አሰላስለው። የዚያን ጊዜም የተከናወነልህና የተሳከልህ ትሆናለህ።
ለምንስ ‘ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ’ ትሉኛላችሁ? ለምናገራቸውስ ነገሮች ለምን አትታዘዙም?
ያዘዝኋችሁን ነገር ብታደርጉ ወዳጆቼ ናችሁ።
ጴጥሮስና ሐዋርያቱ ግን መልሰው፣ “ለሰው ከመታዘዝ ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።
ቀድሞ የኃጢአት አገልጋዮች ነበራችሁ፥ ነገር ግን ለተሰጣችሁ ትምህርት ከልባችሁ ስለ ታዘዛችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን!
ታዛዦች ልጆች እንደ መሆናችሁ ባለማወቅ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ።
እግዚአብሔር አምላካችሁን እንድትወዱ በመንገዱም እንድትሄና ትእዛዙን፥ ሥርዓቱንና ሕጉን እንድትጠብቁ አዝዛችኋል፤ ከዚያም በሕይወት ትኖራላችሁ፥ ትበዛላችሁም፤ አምላካችሁም ትወርሱአት ዘንድ በምትገቡበት ምድር ይባርካችህኋል።