ስለ የእኔ ፈቃድ አይሁን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ የእኔ ፈቃድ አይሁን የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ሉቃስ 22:42

“አባት ሆይ፣ ብትወድ ይህን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፣ ነገር ግን የአንተ ፈቃድ እንጂ የእኔ ፈቃድ አይሁን” በማለት ጸለየ።

02 የማቴዎስ 26:39

ጥቂት ራቅ ብሎ በመሄድ በግንባሩ ወድቆ ጸለየ፤ "አባት ሆይ፣ የሚቻል ከሆነ ይህ ጽዋ ከእኔ ይለፍ፤ ይሁን እንጂ፣ የእኔ ፈቃድ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይሁን" አለ፡፡

03 ዮሐንስ 6:38

ከሰማይ የወረድሁት የራሴን ፈቃድ ለማድረግ ሳይሆን የላከኝን ፈቃድ ለመፈጸም ነውና፡፡

04 ማርቆስ 14:36

አባት ሆይ ለአንተ ሁሉ ይቻላል ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ ነገር ግን የእኔ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይሁን አለ፡፡

05 ፊልጵስዩስ 2:8

እንዲሁም እስከ ሞት፤ያውም እስከ መስቀል ሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ።

06 ዮሐንስ 4:34

ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ «የእኔ ምግብ የላከኝን ፈቃድ ማድረግና ሥራውንም መፈጸም ነው።

07 ዮሐንስ 5:30

እኔ ከራሴ ምንም ማድረግ አልችልም፤ የምፈርደው በሰማሁት መሠረት ነው፤ የላከኝን ፈቃድ እንጂ የራሴን ፈቃድ ስለማልሻም፣ ፍርዴ ትክክል ነው።

08 ዕብራዊያን 10:7

ቀጥሎም፣ “እግዚአብሔር ሆይ በመጽሐፍ ስለ እኔ እንደተጻፈው እነሆ ፈቃድህን ለማድረግ እዚህ አለሁ” ብሏል።

09 ዕብራዊያን 5:8

ምንም እንኳ እርሱ ልጅ ቢሆንም፣ ከደረሰበት መከራ የተነሣ መታዘዝን ተማረ።

አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ ሕግህም ልቤ ውስጥ ነው፡፡

11 ሮሜ 5:19

በአንድ ሰው አለመታዘዝ በኩል ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደሆኑ እንዲሁ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ።

12 1ኛ ጴጥሮስ 2:23

ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራንም ሲቀበል አልዛተም፤ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤

ተዛማጅ ርዕሶች