ስለ ለእግዚአብሔር መገዛት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ለእግዚአብሔር መገዛት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ያዕቆብ 4:7

ስለዚህ፣ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ ዲያብሎስን ተቃወሙት፤ እርሱም ከእናንተ ይሸሻል።

02 ሮሜ 6:13

ከሙታን ሕያው እንደመሆናችሁ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ እንጂ የሰውነት ክፍሎቻችሁን የአመጻ መሣሪያ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ። የሰውነት ክፍሎቻችሁን ለእግዚአብሔር የጽድቅ መሣሪያ አድርጋችሁ አቅርቡ።

03 ያዕቆብ 4:10

በጌታ ፊት ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤ እርሱም ከፍ ያደርጋችኋል።

04 1ኛ ጴጥሮስ 5:6

እርሱ በወሰነው ጊዜ ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከእግዚአብሔር ብርቱ እጅ በታች ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤

05 ሮሜ 12:1

ስለዚህም ወንድሞች ሆይ ሥጋችሁን ህያው መስዋዕት፥ቅዱስ፥ ለእግዚአብሔር የሚገባ አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ምህረት እለምናችኋለሁ፥ ያም ተገቢ የሆነ አገልግሎታችሁ ነው።

ተዛማጅ ርዕሶች