ስለ መንገድ እውነት ሕይወት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ መንገድ እውነት ሕይወት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ዮሐንስ 14:6

ኢየሱስ እንዲህ አለው፤ «እኔ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት ነኝ፤ በእኔ ካልሆነ በቀር ማንም ሰው ወደ አብ ሊመጣ አይችልም።

02 ዮሐንስ 10:9

በሩ እኔ ነኝ። ማንም በእኔ በኩል ቢገባ፣ ይድናል፤ ይገባል፣ ይወጣልም፤ መሰማሪያም ያገኛል።

በሌላ በማንም ድነት የለም፤ ልንድንበት የሚገባ በሰዎች መካከል የተሰጠ ሌላ ስም ከሰማይ በታች የለምና።”

04 ዮሐንስ 11:25

ኢየሱስ፣ “እኔ ትንሣኤና ሕይወት ነኝ፣ በእኔ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፡፡

05 ዕብራዊያን 10:20

ይህም በመጋረጃው ማለትም በሥጋው አማካኝነት ለእኛ የከፈተልን አዲስና ሕያው መንገድ ነው።

06 ዮሐንስ 1:17

ሕግ በሙሴ በኩል ተሰጥቶ ነበር፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ በኩል መጣ፡፡

07 ዮሐንስ 8:32

እውነትን ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነጻ ያወጣችኋል” አላቸው።

08 ዕብራዊያን 10:19-20

ስለዚህ ወንድሞች፣ በኢየሱስ ደም አማካኝነት ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የመግባት ድፍረት አለን። ይህም በመጋረጃው ማለትም በሥጋው አማካኝነት ለእኛ የከፈተልን አዲስና ሕያው መንገድ ነው።

09 ዮሐንስ 6:68

ስምዖን ጴጥሮስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ ‹‹ጌታ ሆይ፣ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤

10 ኤፌሶን 2:18

በኢየሱስ አማካይነት እኛ ሁለታችንም በአንድ መንፈስ ወደ አብ መቅረብ እንችላለንና።

11 1ኛ ዬሐንስ 5:20

እኛ ግን የእግዚአብሔር ልጅ እንደመጣና እውነት የሆነውን እንድናውቅ ማስተዋል እንደሰጠን እናውቃለን፤ እኛም እውነት በሆነው በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ እንዳለን እናውቃለን። እርሱም እውነተኛ አምላክና የዘላለም ህይወት ነው።

ተዛማጅ ርዕሶች