ስለ የክርስቶስ አሳብ በእኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ የክርስቶስ አሳብ በእኛ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ፊልጵስዩስ 2:5

በኢየሱስ ክርስቶስ የነበረ አሳብ በእናንተም ደግሞ ይኑር፤

02 ፊልጵስዩስ 2:6-7

እርሱም የመለኮት ባሕር ነበረው፥ ነገር ግን ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል የሚያደርጋውን የመለኮት ባሕይ እንደ ያዘ አልቆጠረም። ክብሩን ትቶ ራሱን ባዶ አደረገ። የባሪያንም መልክ ያዘ፤ በሰው አምሳል ተገለጠ፤ እንደ ሰውም ሆኖ በትህትና ራሱን ዝቅ አደረገ።

03 1ኛ ቆሮንቶስ 2:16

"የጌታን አሳብ ማን አወቀው፤ ማንስ ሊያስተምረው ይችላል?" እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።

04 ሮሜ 15:5

እንግዲህ የትዕግስትና የመጽናናት አምላክ ለእርስ በእርሳችሁ በክርስቶስ አንድ ልብ ይስጣችሁ።

05 ቆላስይስ 3:2

በላይ ስላሉት ነገሮች እንጂ በምድር ስላሉት ነገሮች አታስቡ።

06 ሮሜ 12:2

መልካም፥ተቀባይነት ያለውና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንድታውቁ በታደስ አዕምሮ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትከትሉ።

07 ፊልጵስዩስ 2:2

ስለዚህ በአንድ አሳብ፤ በፍቅር፤ በመንፈስ አንድነት፤በአንድ ዓላማ እየተስማማችሁ ደስታዬ እንዲፈጸም አድርጉት።

08 1ኛ ጴጥሮስ 4:1

ክርስቶስ በሥጋው መከራን ስለ ተቀበለ፣ እናንተም በዚሁ ዐላማ ታጥቃችሁ ተነሡ፤ በሥጋው መከራን የሚቀበል ሰው ኀጢአትን ትቶአል።

09 ኤፌሶን 4:23

በአእምሮአችሁ መንፈስ እንድትታደሱ

10 ሮሜ 8:5-6

እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ ስለሥጋዊ ነገሮች ያስባሉ፥እንደ መንፈስ ቅዱስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን ስለመንፈስ ቅዱስ ነገሮች ያስባሉ። የሥጋ አስተሳሰብ ሞት ሲሆን የመንፈስ ቅዱስ አስተሳሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።

11 ቆላስይስ 3:1-2

እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ከሞት ካስነሣችሁ፤ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያሉትን ነገሮች እሹ። በላይ ስላሉት ነገሮች እንጂ በምድር ስላሉት ነገሮች አታስቡ።

12 1ኛ ቆሮንቶስ 2:12

እኛ ግን ክእግዚአብሔር በነፃ የተሰጠንን እንድናውቅ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበለንም።

13 ገላቲያ 2:20

ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ። ከእንግዲህ የምኖረው እኔ አይደለሁም፥ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል። አሁን በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና እራሱን ስለ እኔ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።

14 ፊልጵስዩስ 4:8

በመጨረሻም ወንድሞችሆይ፥ እውነት የሆነውን ሁሉ፤ ክቡር የሆነውን ሁሉ፤ ትክክል የሆነውን ሁሉ፤ንጹሕ የሆነውን ሁሉ፤ ፍቅር የሆነውን ሁሉ፤ መልካም የሆነውን ሁሉ፤ በጎነት ቢሆን፤ ምስጋናም ቢሆን፤ እንደ እነዚህ ያሉትን ነገሮች ሁሉ አስቡ።

15 2ኛ ቆሮንቶስ 10:5

ደግሞም በእግዚአብሔር ዕውቀት ላይ የሚነሳውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ፥ እንዲሁም ለክርስቶስ ለመታዘዝ ሀሳብን ሁሉ እንማርካለን።

ተዛማጅ ርዕሶች