ስለ ሌሎችን ማገልገል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ሌሎችን ማገልገል የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ወንድሞች ሆይ እግዚአብሔር የጠራችሁ ለነጻነት ነው። ብቻ ነጻነታችሁን ለሥጋ ፈቃድ አትጠቀሙበት፥ በዚያ ፈንታ እርስ በእርሳችሁ በፍቅር አንዳችሁ አንዳችሁን አገልግሉ።
እንደ ታማኝ የእግዚአብሔር ልዩ ልዩ ጸጋ መጋቢ እያንዳንዱ ሰው በተቀበለው የጸጋ ስጦታ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤
ንጉሡም መልሶ እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ለእነዚህ ታናናሽ ወንድሞቼ ያደረጋችሁትን ለእኔ አድርጋችሁታል።’
ምክንያቱም ቅዱሳንን በማገልገላችሁና አሁንም እያገለገላችኋቸው በመሆኑ ለስሙ ያላችሁን ፍቅር በማሳየት የሠራችሁትን ሥራ ይረሳ ዘንድ እግዚአብሔር ዓመፀኛ አይደለም።
ልግምተኞች አትሁኑ፤በመንፈሳችሁ ንቁ ሁኑ ፥ ጌታንም አገልግሉ።
ስለዚህም ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ለሰው ሁሉ በተለይም ለእምነት ቤተሰቦች መልካምን እናድርግ።
የሰው ልጅም ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊያደርግ እንጂ እንዲያገልግሉት አልመጣም አላቸው፡፡
እኔ ጌታና መምህር ሆኜ እግራችሁን ካጠብሁ፣ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ልትተጣጠቡ ይገባል።
እንዲሁም እያንዳንዳእሁ የራሳችሁን ጥቅም ብቻ ሳይሆን የሌላውንም ሰው ጥቅም አስቡ።
ደካሞችን በሥራ እንዴት እንደምትረዱ፣ “ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ የተባረከ ነው” የሚለውንም የጌታ ኢየሱስን ቃል እንዴት እንደምታስታውሱ በሁሉም ረገድ አርኣያ ሆንኋችሁ።
ደግሞም ለእያንዳንዱ መንፍስ ቅዱስን መግለጥ የተሰጠው ለሁሉም ጥቅም ሲባል ነው።
በእናንተ መካከል ግን እንዲህ መደረግ የለበትም። ይልቁንም፣ ከእናንተ መካከል ታላቅ ሊሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋያችሁ ይሁን፤ ከእናንተም ፊተኛ ሊሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋያችሁ ይሁን።
ሰውን ሳይሆን ጌታን እንደምታገለግሉ እያሰባችሁ በደስታ አገልግሉ።