ስለ የዋህነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ የዋህነት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ደግነታችሁ በሰዎች ሁሉ ዘንድ ይታወቅ።
የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፣ ሠላም፣ ትዕግሥ፣ ቸርነት፥ መልካምነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ናቸው። ህግ እነዚህን አይቃወም።
ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳንና የተወደዳችሁ ሆናችሁ ርኅራኄን፣ ቸርነትን፣ ትሕትናን፣ ገርነትን፣ ትዕግሥትን ልበሱ።
የለዘበ መልስ ቁጣን ይመልሳል፣ መጥፎ ቃል ግን ቁጣን ያስነሳል፡፡
የጌታ አገልጋይ ሊጣላ አይገባውም፣ ከዚሀ ይልቅ ለሁሉ የሚጠነቀቅ፣ ለማስተማርም የሚበቃ በትእግስትም የሚጸና፣
ማንንም እንዳይሳደቡ፣ የሌሎችንም ፈቃድ እንዲያከብሩ እንጂ እንዳይከራከሩ፣ ለሁሉም ሰው ትህትን እንዲያሳዩ አሳስባቸው።
ይልቁንም፣ ክርስቶስ የከበረ መሆኑን ተረድታችሁ በልባችሁ ቀድሱት። እናንተ በእግዚአብሔር ላይ ስላላችሁ መታመን ምክንያቱን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁል ጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን ይህን ሁሉ በትሕትናና በአክብሮት አድርጉት፤
ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ፣ ከእኔም ተማሩ፣ እኔ የዋህና በልቤ ትሁት ነኝ፣ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፡፡
ይኽውም እርስ በርስ በፍቅር ተቻችላችሁ በፍጹም ትሕትና፥በገርነትና በትዕግሥት እንድትኖሩ ነው።
አንተ ግን፣ የእግዚአብሔር ሰው፣ ከእነዚሀ ነገሮች ሽሽ፡፡ ጽድቅን፣ እግዚአብሔርን መምሰል፣ ታማኝነትን፣ ፍቅርን፣ ጽናትን እና ለሰዎች መጠንቀቅን ተከታተል፡፡
ከላይ የሚመጣው ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጹሕ ነው፤ ከዚያም ሰላም ወዳድ፣ ጨዋ፣ ደግ፣ ምሕረትና መልካም ፍሬ የሞላበት፣ ለሰዎች አድልዎ የማያደርግ ቅን ነው።
በትዕግስት ገዢን እንዲለዝብ ማድረግ ይቻላል፣ መልካም ምላስም አጥንትን ትሰብራለች፡፡
ይልቁንም እናት የራስዋን ልጆች እንደምትንከባከብ በመካከላችሁ የዋሆች ሆንን።
መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፣ ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል፣ የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል።