ስለ ትሕትና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ትሕትና የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ፊልጵስዩስ 2:3

በራስ ወዳድነት ወይም በከንቱ ትምክህት ምንም አታድርጉ፤ነገር ግን በዚህ ፈንታ ሌሎች ሰዎች ከእናንተ እንደሚሻሉ በትህትና ቁጠሩ።

02 ያዕቆብ 4:6

እግዚአብሔር ግን አብዝቶ ጸጋውን ይሰጣል፤ መጽሐፍ፣ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” የሚለው በዚህ ምክንያት ነው።

03 ምሳሌ 22:4

የትህትናና እግዚአብሔርን የመፍራት ሽልማት ባለጠግነት፣ ክብርና ሕይወት ነው፡፡

ሰው ሆይ፣ መልካሙን፣ ያህዌ ከአንተ የሚፈልገውን ነግሮሃል ፍትሕ አድርግ፤ ደግነትን ውደድ፤ ከአምላክህ ጋር በትሕትና ተመላለስ፡፡

05 ሮሜ 12:3

ከእናንተ ማንም ስለራሱ ሊያስብ ከሚገባው በላይ እንዳያስብ በተሰጠኝ ጸጋ አሳስብለሁ። ይልቁኑም ለእያንዳንዱ ከእግዚአብሔር በተሰጠው እምነት ልክ በጥበብ ሊያስብ ይገባል።

06 1ኛ ጴጥሮስ 5:5

ጕልማሶች ሆይ፤ እናንተም እንዲሁ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ ምክንያቱም፣ «እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል» እንደ ተባለው፣

07 ምሳሌ 11:2

ትዕቢት ከመጣች ውርደት ትመጣለች፣ ከትህትና ጋር ግን ጥበብ ትመጣለች፡፡

08 ምሳሌ 15:33

የእግዚአብሔር ፍርሃት ጥበብን ያስተምራል፣ ትህትናም ከክብር በፊት ትመጣለች፡፡

09 ቆላስይስ 3:12

ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳንና የተወደዳችሁ ሆናችሁ ርኅራኄን፣ ቸርነትን፣ ትሕትናን፣ ገርነትን፣ ትዕግሥትን ልበሱ።

ተዛማጅ ርዕሶች