ስለ በመንግሥቱ ውስጥ ታላቅነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ በመንግሥቱ ውስጥ ታላቅነት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 የማቴዎስ 20:26

በእናንተ መካከል ግን እንዲህ መደረግ የለበትም። ይልቁንም፣ ከእናንተ መካከል ታላቅ ሊሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋያችሁ ይሁን፤

02 የማቴዎስ 23:11

ከእናንተ መካከል ታላቅ የሆነው አገልጋያችሁ ይሁን፡፡

03 ማርቆስ 9:35

ተቀምጦም አሥራ ሁለቱን ጠራቸው፣ እንዲህም አላቸው፣ ከእናንተ የመጀመሪያ ሊሆን የሚወድ የሁሉ መጨረሻና አገልጋይ ይሁን፤

04 ሉቃስ 22:26

ነገር ግን በእናንተ ዘንድ እንዲህ አይሁን። ይልቅ ከእናንተ ታላቅ የሆነ እንደ ታናሽ ይሁን። እጅግ ተፈላጊ የሆነ እንደሚያገለግል ሰው ይሁን።

05 የማቴዎስ 18:4

ስለዚህ እንደዚህ ልጅ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሰው ሁሉ፣ እንዲሁ በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ይበልጣል፡፡

06 የማቴዎስ 18:3

እንዲህም አለ፡- "እውነት እላችኋለሁ፤ ንስሐ ካልገባችሁና እንደ ልጆች ካልሆናችሁ በምንም መንገድ ወደ መንግሥተ ሰማያት አትገቡም፡፡

07 ሉቃስ 9:48

"እንደዚህ ያለውን ሕፃን በስሜ የሚቀበል፣ እኔን ይቀበላል። እኔን የሚቀበል ከሆነ ደግሞ የላከኝን ይቀበላል። ስለሆነም፣ በመካከላችሁ ከሁላችሁም የሚያንስ እርሱ ታላቅ ነውና።”

08 የማቴዎስ 20:27

ከእናንተም ፊተኛ ሊሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋያችሁ ይሁን።

09 ማርቆስ 10:43-44

በእናንተ ዘንድ ግን እንዲህ አይደለም ነገር ግን ከእናንተ ማንም የበላይ(ታላቅ) ለመሆን የሚፈልግ የሁሉ አገልጋይ ይሁን ፊተኛ ለመሆን የሚፈልግም የሁሉ ባሪያ ይሁን

ተዛማጅ ርዕሶች