ስለ እግዚአብሔር ፈዋሻችን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ እግዚአብሔር ፈዋሻችን የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
እንዲህ አለ፤ “የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ድምፅ በጥንቃቄ ብትሰሙ፥ ትክክለኛ የሆነውንም በፊቱ ብታደርጉ፣ ትእዛዛቱንም ብታስተውሉና ሕግጋቱን ሁሉ ብትጠብቁ፣ ግብፃውያን ላይ ካመጣኋቸው በሽታዎች አንዱንም በእናንተ ላይ አላመጣም፤ እኔ ፈዋሻችሁ እግዚአብሔር ነኝና።”
ነፍሴ ሆይ፣ ያህዌን አመሰግኚ ውለታውንም ሁሉ አትርሺ፡፡ ኃጢአትሽን ሁሉ ይቅር ይላል ደዌሽንም ሁሉ ይፈውሳል፡፡
እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፣ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፣ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
እግዚአብሔር ሆይ፣ ፈውሰኝ እኔም እፈወሳለሁ! አድነኝ እኔም እድናለሁ። አንተ የምስጋናዬ ዝማሬ ነህና።
ልባቸው የተሰበረውን ይፈውሳል ቁስላቸውንም ይጠግናል፡፡
እኔ ጤናሽን እመልስልሻለሁ ቍስልሽንም እፈውሳለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ይህንንም የማደርገው፦ ማንም የማይሻት፤ የተጣለች ጽዮን" ብለው ጠርተውሻልና።
ያህዌ ሆይ፣ እንድትረዳኝ ወደ አንተ ጮኽሁ አንተም ፈውሰኸኝ፡፡
ስሜን ለምትፈሩ ለእናንተ ግን ፈውስ በክንፎቹ የያዘ የጽድቅ ፀሐይ ይወጣላቸዋል። እናንተም ከጋጥ እንደተለቀቁ እንቦሳ እየቦረቃችሁ ትወጣላችሁ።
እናንተ ደካሞች፣ ሸክም የከበዳችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፣ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋላሁ፡፡
ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በመስቀል ላይ ተሸከመ፤ በእርሱ ቊስል እናንተ ተፈውሳችኋል።
ታሞ በተኛበት አልጋ ያህዌ ይንከባከበዋል በበሽታውም ጊዜ መኝታውን ያነጥፍለታል፡፡
ኑ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ። እርሱ ገነጣጥሎናል፥ ነገር ግን እርሱ ይፈውሰናል፤ እርሱ አቁስሎናል፥ ነገር ግን እርሱ ቁስላችንን አስሮ ይጠግናል።
“ለድሆች የምሥራቹን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለምርኮኞች ነፃነትን፣ ለዕውሮች ብርሃናቸው እንደሚመለስላቸው ፣ የተጨቆኑትም መፈታትን እንደሚያገኙ
ቃሉን ልኮ ፈወሳቸው፡፡ ከመቃብር አፋፍ መለሳቸው፡፡
በእናንተ መካከል የታመመ አለ? የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ይጥራ፤ እነርሱም በጌታ ስም ዘይት እየቀቡ ይጸልዩለት፤ የእምነት ጸሎት የታመመውን ሰው ይፈውሳል፤ ጌታም ያስነሣዋል። ኃጢአት አድርጎ ከሆነም እግዚአብሔር ይቅር ይለዋል።