ስለ እርግማን መወገድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ እርግማን መወገድ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ገላቲያ 3:13

«በእንጨት ላይ የሚሰቀል የተረገመ ነው» ተብሎ በተጻፈው መሰረት እርሱ ስለኛ እርግማን በመሆን ከህግ እርግማን ዋጀን።

02 ሮሜ 8:1

ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም።

03 ቆላስይስ 2:14

እርሱ ይከሰን የነበረውን የዕዳ ጽሑፍ ደመሰሰው። ሁሉንም በመስቀል ላይ ቸንክሮ ከእኛ አስወገደው።

04 1ኛ ጴጥሮስ 2:24

ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በመስቀል ላይ ተሸከመ፤ በእርሱ ቊስል እናንተ ተፈውሳችኋል።

ከእንግዲህ ምንም ዐይነት መርገም አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉ ዚፋን ከተማው ውስጥ ይሆናሉ፤ አገልጋዮቹም ያገለግሉታል።

እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ሞት፣ ወይም ሐዘን፣ ወይም ለቅሶ ወይም ሕመም አይኖርም። ምክንያቱም የቀድሞ ነገሮች አልፈዋል።

07 2ኛ ቆሮንቶስ 5:21

እኛም በእርሱ የእግዚአብሔር ፅድቅ እንድንሆን ሃጢያት ሰርቶ የማያውቀውን ክርስቶስን እግዚአብሔር የሃጢያት መስዋዕት አደረገው።

ተዛማጅ ርዕሶች